2 ቆሮንቶስ 1:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተ ጋር በክርስቶስ ስም የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ፣ እኛንም እናንተንም በክርስቶስ ጸንተን እንድንቆም የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው፤ የቀባንም እርሱ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በክርስቶስ ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛን ከእናንተ ጋር በክርስቶስ እንድንጸና ያደረገን እግዚአብሔር ነው፤ ለሥራ የለየንም እርሱ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥ |
እንደ ተገደሉና በመቃብር ውስጥ እንደ ተጣሉ፥ ለዘለዓለም እንደማታስባቸው በሙታን መካከል የተጣልሁ ሆንሁ፤ እነርሱ ከእጅህ ርቀዋልና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በተመረጠችው ዕለት ሰምቼሃለሁ፤ ድኅነት በሚደረግበትም ቀን ረድቼሃለሁ፤ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትን ርስቶች ትወርስ ዘንድ፤
“ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይጠፋም፥” ይላል እግዚአብሔር።
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
እግዚአብሔርን በክህነት ያገለግሉት ዘንድ በተቀቡበት ቀን ለእግዚአብሔር ከሆነ ከእሳት ቍርባን የአሮንና የልጆቹ ሕግ ይህ ነው።
ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው፥ እየዞረም መልካም እንደ አደረገ፥ ሰይጣን ያሸነፋቸውንም እንደ ፈወሰ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና።
ይህም በነቢያት ቃልና የዘለዓለም ገዥ በሚሆን በእግዚአብሔር ትእዛዝ በዚህ ወራት ተገለጠ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተውና ዐውቀው በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ያምኑ ዘንድ።
እናንተ ግን ለመንፈሳዊ ሕግ እንጂ ለሥጋችሁ ፈቃድ የምትሠሩ አይደላችሁም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ አድሮ ይኖራልና፤ የክርስቶስ መንፈስ ያላደረበት ግን እርሱ የእርሱ ወገን አይደለም።
ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ፤ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችሁማል፤ ያበረታችሁማል።
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።
ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዐይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ።