Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 7:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በተ​ቀ​ቡ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆነ ከእ​ሳት ቍር​ባን የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ በቀረቡ ቀን፣ በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው መሥዋዕት ላይ ለአሮንና ለልጆቹ የተመደበላቸው ድርሻ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 “ጌታን በክህነት እንዲያገለግሉት እነርሱን ባቀረባቸው ቀን ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ይህም እግዚአብሔር አሮንንና ልጆቹን ካህናት አድርጎ በሾመበት ቀን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ከሚቃጠል መሥዋዕት ለካህናት ድርሻ ሆኖ የተለየ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እግዚአብሔርን በክህነት ያገለግሉት ዘንድ ባቀረባቸው ቀን ለእግዚአብሔር ከሆነ ከእሳት ቁርባን የአሮንና የልጆቹ እድል ፈንታ ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 7:35
15 Referencias Cruzadas  

“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን አሮ​ንን ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆ​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ​ተህ በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ አንተ አቅ​ርብ፤ አሮ​ንን የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች፥ ናዳ​ብን፥ አብ​ዩ​ድ​ንም፥ አል​ዓ​ዛ​ር​ንም ኢታ​ም​ር​ንም አቅ​ርብ።


“እኔ​ንም በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ሁለት አውራ በጎች ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ካለው ደም ከቅ​ብ​ዐት ዘይ​ትም ወስ​ደህ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ባሉት በል​ጆ​ቹና በል​ብ​ሶ​ቻ​ቸው ላይ ትረ​ጨ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ልብ​ሶ​ቹም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ልጆቹ፥ ልብ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይቀ​ደ​ሳሉ።


የቅ​ብ​ዐ​ት​ንም ዘይት ወስ​ደህ በራሱ ላይ ታፈ​ስ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ው​ማ​ለህ።


በዚ​ያም ቀን ቀን​በሩ ከጫ​ን​ቃህ፥ ፍር​ሀ​ቱም ከአ​ንተ ላይ ይወ​ር​ዳል፤ ቀን​በ​ሩም ከጫ​ን​ቃህ ወርዶ ይሰ​በ​ራል።


የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እሰ​ብክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ኛ​ልና፤ ልባ​ቸው የተ​ሰ​በ​ረ​ውን እጠ​ግን ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን፥ ለታ​ሰ​ሩ​ትም መፈ​ታ​ትን፥ ለዕ​ው​ራ​ንም ማየ​ትን እና​ገር ዘንድ ልኮ​ኛል።


ሙሴም ከቅ​ብ​ዐቱ ዘይ​ትና በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ከአ​ለው ከደሙ ወስዶ በአ​ሮ​ንና በል​ብሱ ላይ ፥ በል​ጆ​ቹና በል​ጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮ​ን​ንና ልብ​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የል​ጆ​ቹ​ንም ልብስ ቀደሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይና​ገ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን ሰፍሮ አይ​ሰ​ጥ​ምና።


ከእ​ና​ንተ ጋር በክ​ር​ስ​ቶስ ስም የሚ​ያ​ጸ​ና​ንና የቀ​ባን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።


እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆ​ነኝ ዘንድ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣ​ን​ንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉ​ድ​ንም በፊቴ ይለ​ብስ ዘንድ፥ የአ​ባ​ት​ህን ቤት ለእኔ መረ​ጥ​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች የእ​ሳት ቍር​ባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአ​ባ​ትህ ቤት ሰጠሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos