ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊትንም፥ “ሂድ፤ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ በላያቸው አስነሣው።
2 ዜና መዋዕል 32:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስ ግን እግዚአብሔር እንደ ሰጠው ቸርነት መጠን አላደረገም፤ ልቡም ኮራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ ቍጣ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቅያስ ልብ ግን ታበየ እንጂ ስለ ተደረገለት በጎ ነገር ተገቢ ምላሽ አልሰጠም፤ በዚህ ምክንያት የእግዚአብሔር ቍጣ በርሱ፣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስ ግን እንደ ተቀበለው ቸርነት መጠን አላደረገም፥ ልቡም ኰራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ በኢየሩሳሌምም ላይ ቁጣ ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስ ግን ልቡ በትዕቢት ተሞልቶ ስለ ነበር፥ እግዚአብሔር ስላደረገለት ቸርነት ሁሉ ተገቢ ምስጋና አላቀረበም፤ ከዚህም የተነሣ በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሕዝብ ብርቱ ሥቃይ ደረሰባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስ ግን እንደ ተቀበለው ቸርነት መጠን አላደረገም፤ ልቡም ኳራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ በኢየሩሳሌምም ላይ ቍጣ ሆነ። |
ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ ዳዊትንም፥ “ሂድ፤ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ በላያቸው አስነሣው።
ኤዶምያስን በእውነት መታህ፤ ልብህንም ከፍ ከፍ አደረግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤትህም ተቀመጥ፤ አንተ፥ ይሁዳም ከአንተ ጋር ትወድቁ ዘንድ ስለ ምን መከራን ትሻለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ላከ።
በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ መሮዳህ ሕዝቅያስ እንደ ታመመ ሰምቶ ነበርና የበልዳንን ልጅ በልዳንን ከመጻሕፍትና እጅ መንሻ ጋር ወደ ሕዝቅያስ ላከ።
ሕዝቅያስም በእነርሱ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱንም ሁሉ፥ ብሩንና ወርቁንም፥ ሽቱውንና የከበረውንም ዘይት፥ መሣሪያም ያለበትን ቤት በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
ነቢዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን፥ “ኀጢአተኛውን ታግዛለህን? ወይስ እግዚአብሔር የሚጠላውን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቍጣ መጥቶብሃል።
የአባቶቻቸውንም አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው ባዕድ አምላክንና ጣዖታትን አመለኩ፤ በዚያም ወራት በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቍጣ ወረደ።
አንተም፦ እነሆ፥ ኤዶምያስን መትቻለሁ ብለህ በልብህ ኰርተሃል፤ በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተ ከይሁዳ ጋር ትወድቅ ዘንድ ስለምን መከራን በራስህ ትሻለህ?”
ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፤ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ።
ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በሀገሩ ላይ ስለ ተደረገው ተአምራት ይጠይቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተላኩ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።
በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻን፥ መልእክተኞችንም ላከለት።
ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እጅግ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱንም፥ ወርቁንና ብሩን፥ ከርቤውንና ዕጣኑን፥ ዘይቱንም፥ መሣሪያም ያለበትን ቤት ሁሉ፥ ልብሱንና ዕንቍውን ሁሉ፥ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
በውበትህ ምክንያት ልብህ ኰርቶአል፤ ከክብርህ የተነሣ ጥበብህን አረከስህ፤ በምድር ላይ ጣልሁህ፤ ያዩህም፥ ይዘብቱብህም ዘንድ በነገሥታት ፊት አሳልፌ ሰጠሁህ።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስን አለቃ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርትዋል፥ አንተ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እግዚአብሔርም በባሕር መካከል እንዲቀመጥ እኔም ተቀምጫለሁ ብለሃልና፤ አንተ ሰው ስትሆን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ እግዚአብሔር አይደለህም።
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቁመትህ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ ራስህም በደመናት መካከል ደርሶአልና፤ ትዕቢቱንም አየሁ፤
ደንቆሮ፥ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ይህን ትመልሳለህን? የፈጠረህ አባትህ አይደለምን? የፈጠረህና ያጸናህ እርሱ ነው።