ሮቤልም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ብላቴናውን አትበድሉ ብዬአችሁ አልነበረምን? እኔንም አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈላለጋችኋል።”
2 ዜና መዋዕል 24:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ አባቱ ኢዮአዳ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ ልጁንም አዛርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፥ “እግዚአብሔር ይየው፤ ይፍረደውም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ በዚህ ፈንታ ልጁን ገደለው፤ በሚሞትበትም ጊዜ፣ “እግዚአብሔር ይየው፤ እርሱው ይበቀልህ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፥ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፦ “ጌታ ይየው፥ ይበቀለውም” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቅን አገልግሎት በመዘንጋት ዘካርያስን ገደለ፤ ዘካርያስም ሊሞት ሲያጣጥር ሳለ “እግዚአብሔር ይህን ግፍ ተመልክቶ ይቅጣህ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት “እግዚአብሔር ይየው፤ ይፈልገውም” አለ። |
ሮቤልም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ብላቴናውን አትበድሉ ብዬአችሁ አልነበረምን? እኔንም አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህ እነሆ፥ አሁን ደሙ ይፈላለጋችኋል።”
ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።
ኵላሊትንና ልብን የምትፈትን፥ በቅንም የምትፈርድ እግዚአብሔር ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ከእነርሱ ፍረድልኝ።
ጥፋት በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ተዋጊዎችዋ ተያዙ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እግዚአብሔር ተበቅሎአቸዋልና፥ እግዚአብሔርም ፍዳን ከፍሎአቸዋልና።
ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ገደሉት እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ እውነት እላችኋለሁ ከዚች ትውልድ ይፈለጋል።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ በየትኛው ሥራ ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?”
አምላካችንን እግዚአብሔርን እንድንክደው፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህልን ቍርባን እንድናሳርግበት፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት መሠዊያ ሠርተን እንደ ሆነ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ይመራመረን፤
እርሱም ለእስራኤል በጎ ነገርን ሁሉ እንዳደረገ መጠን፥ እነርሱ ይሩበኣል ለተባለው ለጌዴዎን ቤት ወረታ አላደረጉም።