Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 24:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፥ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፦ “ጌታ ይየው፥ ይበቀለውም” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ በዚህ ፈንታ ልጁን ገደለው፤ በሚሞትበትም ጊዜ፣ “እግዚአብሔር ይየው፤ እርሱው ይበቀልህ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ንጉሥ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቅን አገልግሎት በመዘንጋት ዘካርያስን ገደለ፤ ዘካርያስም ሊሞት ሲያጣጥር ሳለ “እግዚአብሔር ይህን ግፍ ተመልክቶ ይቅጣህ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እን​ዲ​ሁም ንጉሡ ኢዮ​አስ አባቱ ኢዮ​አዳ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቸር​ነት አላ​ሰ​በም፤ ልጁ​ንም አዛ​ር​ያ​ስን አስ​ገ​ደ​ለው፤ እር​ሱም ሲሞት፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይየው፤ ይፍ​ረ​ደ​ውም” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት “እግዚአብሔር ይየው፤ ይፈልገውም” አለ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 24:22
19 Referencias Cruzadas  

ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።


ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት እና ከሰውም ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።


አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቁጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፥ ምስኪን እራሱን ለአንተ አሳልፎ ይሰጣል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።


በፍቅሬ ፋንታ ከሰሱኝ፥ እኔ ግን እጸልያለሁ።


ደምን የሚበቀል እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።


በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም።


ነገር ግን ኩላሊትንና ልብን የምትመረምር በቅንም የምትፈርድ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ሙግቴን ገልጬልሃለሁና በእነርሱ ላይ የሚሆነውን በቀልህን ልይ።


አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ ጌታ ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።


ይህም ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ ነው። አዎን እላችኋለሁ፤ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል።


ኢየሱስ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ የትኛው ሥራ ትወግሩኛላችሁ?” ብሎ መለሰላቸው።


የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ ብዙ ክፉ ነገሮችን አድርጎብኛል፤ ጌታ እንደ ሥራው ብድራቱን ይከፍለዋል።


በመጀመሪያው ሙግቴ አንድም ሰው እንኳ ከጎኔ አልቆመም፤ ሁሉም ግን ከዱኝ፤ ይህንንም በደል በእነርሱ ላይ አይቁጠርባቸው፤


ጌታን ከመከተል እንድንመለስ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህል ቁርባን እንድናሳርግበት፥ የአንድነትንም መሥዋዕት እንድናቀርብበት ብለን መሠዊያ ሠርተን እንደሆነ ጌታ እርሱ ራሱ ይበቀለን፤


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና፤ በዝሙትዋ ምድርን ያበላሸችውን ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባት፥ የባርያዎቹንም ደም ከእጅዋ ተበቀሎአልና።


እንዲሁም ይሩባኣል የተባለው ጌዴዎን ያደረገላቸውን በጎ ነገር ሁሉ አስበው ለቤተ ሰቡ ውለታ መላሽ ሆነው አልተገኙም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos