የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት።
2 ዜና መዋዕል 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራትን ይሰጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ እግዚአብሔር የዳዊትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አልወደደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋራ ካደረገው ኪዳን የተነሣ፣ የዳዊትን ቤት ማጥፋት አልፈለገም፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም መብራት እንደሚሰጥ ተስፋ ሰጥቶ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ለመስጠት ስላደረገው ተስፋ፥ ጌታ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ እግዚአብሔር የዳዊትን ሥርወ መንግሥት ሊያጠፋ አልፈለገም፤ ይህም የሆነው እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ከዳዊት ጋር ቃል ኪዳን ገብቶ ስለ ነበርና የዳዊት ዘሮችም ዘወትር ሳያቋርጡ የሚነግሡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተስፋ ቃል ሰጥቶት ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከዳዊት ጋር ስላደረገው ቃል ኪዳን፥ ለእርሱና ለልጆቹም በዘመናት ሁሉ መብራት ይሰጠው ዘንድ ስለ ሰጠው ተስፋ፥ እግዚአብሔር የዳዊትን ቤት ያጠፋ ዘንድ አልወደደም። |
የሶርህያም ልጅ አቢሳ አዳነው፤ ፍልስጥኤማዊውንም ወግቶ ገደለው። ያንጊዜም የዳዊት ሰዎች፥ “አንተ የእስራኤል መብራት እንዳትጠፋ ከእንግዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰልፍ አትወጣም” ብለው ማሉለት።
በውኑ ቤቴ በኀያሉ ዘንድ እንዲሁ አይደለምን? ከእኔም ጋር በዘመኑ ሁሉ የተዘጋጀና የተጠበቀ፥ የዘለዓለም ቃል ኪዳን አድርጎአል፤ መድኀኒቴም ፈቃዴም ሁሉ ይህ ነውና። ዐመፀኛም አይበቅልምና።
ነገር ግን ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊትና ስለ መረጥኋት ሀገሬ ስለ ኢየሩሳሌም ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጣለሁ እንጂ መንግሥቱን ሁሉ አልከፍልም።”
ስሜንም ባኖርሁባት በዚያች በመረጥኋት ከተማ በኢየሩሳሌም ለባሪያዬ ለዳዊት በፊቴ ሁልጊዜ መብራት ይሆንለት ዘንድ ለልጁ ሁለት ነገድን እሰጠዋለሁ።
ነገር ግን ልጁን ከእርሱ በኋላ ያስነሣ ዘንድ፥ ኢየሩሳሌምንም ያጸና ዘንድ አምላኩ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት በኢየሩሳሌም መብራትን አደረገለት፤
ነገር ግን ለእርሱና ለልጆቹ በዘመኑ ሁሉ መብራት ይሰጠው ዘንድ ተስፋ እንደ አደረገለት፥ ስለ ባሪያው ስለ ዳዊት እግዚአብሔር ይሁዳን ያጠፋ ዘንድ አልወደደም።
ኢዮራምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በአባቱም በዳዊት ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ በፋንታውም ልጁ አካዝያስ ነገሠ።
የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት ግን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ሰርቃ ወሰደች፤ እርሱንና ሞግዚቱን በእልፍኝ ውስጥ አኖረቻቸው፤ የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት ከጎቶልያ ፊት ሸሸገችው፤ እርስዋም አልገደለችውም።
የይሁዳም ጉባኤ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከንጉሥ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። የንጉሥንም ልጅ አሳያቸው፤ አላቸውም፥ “እነሆ፥ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ቤት እንደ ተናገረ የንጉሡ ልጅ ይነግሣል።
አሁንም አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆችህ በሕጌ ይሄዱ ዘንድ መንገዳቸውን ቢጠብቁ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው በፊቴ አይታጣም ብለህ የተናገርኸውን ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት ጠብቅ፤ አጽናም።