ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፤ ከርኵሰቷም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመለሰች።
2 ዜና መዋዕል 16:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳም በነቢዩ በአናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በግዞት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አስጨነቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የተነሣም አሳ ባለራእዩን ተቈጣው፤ በጣም ስለ ተናደደም እስር ቤት አስገባው። በዚያ ጊዜም አሳ አንዳንድ ሰዎችን ክፉኛ አስጨነቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በቊራኛ አስሮ በወህኒ ቤት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ፥ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አሠቃየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ አነጋገር አሳን እጅግ ስላስቈጣው ነቢዩን በብረት ሰንሰለት አስሮ ወህኒ አስገባው፤ ከዚህም ጊዜ አንሥቶ፥ ንጉሥ አሳ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹን በጭካኔ ማንገላታት ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳም በባለ ራእዩ ላይ ተቈጣ፤ ስለዚህም ነገር ተቈጥቶአልና በግዞት አኖረው፤ በዚያን ጊዜም አሳ ከሕዝቡ አያሌ ሰዎችን አስጨነቀ። |
ዳዊትም መልእክተኞችን ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፤ ከርኵሰቷም ነጽታ ነበርና ከእርስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመለሰች።
ዳዊትም ናታንን፥ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው። ናታንም ዳዊትን አለው፥ “እግዚአብሔር ደግሞ ኀጢአትህን አርቆልሃል፤ አትሞትምም።
በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቈፈሪያ በብረት መጥረቢያም ሥር አኖራቸው፤ በሸክላ ጡብ እቶንም አሳለፋቸው። በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ዳዊትም፥ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኢዮርብዓም የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ የተናገረውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ንጉሡ፥ “ያዙት” ብሎ እጁን ከመሠዊያው ላይ አነሣ። ከዚህም በኋላ በእርሱ ላይ የዘረጋት እጁ ደረቀች፤ ወደ እርሱም ይመልሳት ዘንድ አልተቻለውም።
ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውኃ አጠጡት በሉአቸው” አለ።
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
እንዲህም በሉአቸው፦ ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውኃ አጠጡት።”
እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
ዖዝያንም ተቈጣ፤ በመቅደስም የሚያጥንበት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህናቱንም በተቈጣ ጊዜ በካህናቱ ፊት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ ሳለ በግንባሩ ላይ ለምጽ ታየ።
ወደ በደሉሽና ወደ አጐሰቈሉሽ ሰዎች እጅ፥ ሰውነትሽንም ዝቅ በዪ፥ ድልድይ አድርገን እንሻገርብሽ ወደሚሏት ሰዎች እጅ እመልሰዋለሁ።” በምድርም ላይ በሆድሽ አስተኙሽ፤ መንገደኞችም ሁሉ ረገጡሽ።
ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን ገረፈው፤ በእግዚአብሔርም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው አዘቅት ውስጥ ጣለው።
ንጉሡም ኢዮአቄም፥ ሠራዊቱ ሁሉ፥ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኡርያም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ፤ ወደ ግብፅም ገባ።
ትንቢት የሚናገረውን ሰው ሁሉ፥ የሚለፈልፈውንም ሰው ሁሉ በግዞት ታኖረውና በፈሳሽም ታሰጥመው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።