1 ጢሞቴዎስ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ከሁሉ በፊት እንዲደረጉ የምመክረው ነገር ቢኖር ልመናና ጸሎት፥ ምልጃና ምስጋና ስለ ሰዎች ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን በማምለክና ክብር በተመላ ሕይወት ልመና፥ ጸሎት፥ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። |
በእርስዋ ሰላም፥ ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማረክኋችሁ ሀገር ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።”
የቀድሞውንስ ያለ ማወቅ ዘመን እግዚአብሔር አሳልፎታል፤ ዛሬ ግን በመላው ዓለም ንስሓ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዝዞአል።
አስቀድሜ ስለ ሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ፤ ማመናችሁ በዓለም ሁሉ ተሰምታለችና።
የኀጢአት ተገዦች ስትሆኑ ምሳሌነቱ ለተሰጣችሁ ለምትማሩት ትምህርት ታዝዛችኋልና እግዚአብሔር ይመስገን።
ጌታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ፥ በአምላካችንና በአባታችን ፊት በቅድስና ነቀፋ የሌለበት አድርጎ ልባችሁን ያጸና ዘንድ፥ እኛ ደግሞ ለእናንተ እንደምንሆን ጌታ እርስ በእርሳችሁ ያላችሁን ለሁሉም የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ፤ ይጨምርም።
ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ፥ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤