Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይኸ​ውም ለሰ​ማይ አም​ላክ በጎ መዓዛ የሆ​ነ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ዘንድ፥ ለን​ጉ​ሡና ለል​ጆ​ቹም ዕድሜ ይጸ​ልዩ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ይህ የሚሆነው የሰማይ አምላክን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ ለንጉሡና ለወንድ ልጆቹም ደኅንነት እንዲጸልዩ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይህም ለሰማያት አምላክ መልካም መዓዛ እንዲያቀርቡ፥ ለንጉሥና ለልጆቹ ሕይወትም እንዲጸልዩ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ይህም ሁሉ የሚሆንበት ምክንያት የሰማይ አምላክ በደስታ የሚቀበለውን መሥዋዕት ሁሉ በማቅረብ ለእኔና ለልጆቼ ሕይወት እንዲጸልዩልን ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይኸውም ለሰማይ አምላክ ጣፋጭ ሽቱ የሆነውን መሥዋዕት ያቀረቡ ዘንድ ለንጉሥና ለልጆቹም ዕድሜ ይጸልዩ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 6:10
11 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም።


“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤


ለሰ​ማይ አም​ላክ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን ወይ​ፈ​ኖ​ችና አውራ በጎች፥ ጠቦ​ቶ​ችም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እን​ዳሉ እንደ ካህ​ናቱ ቃል ስን​ዴና ጨው፥ የወ​ይን ጠጅና ዘይት የሚ​ጠ​ይ​ቋ​ች​ሁን ዕለት ዕለት ስጡ​አ​ቸው።


በን​ጉሡ መን​ግ​ሥ​ትና በል​ጆቹ ላይ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ የሰ​ማይ አም​ላክ ያዘ​ዘው ሁሉ ይደ​ረግ፤ ለሰ​ማይ አም​ላክ ቤት የታ​ዘ​ዘ​ው​ንም እን​ዳ​ታ​ቋ​ርጡ ተጠ​ን​ቀቁ።


በጎ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ላሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ውሰዱ፤ ሂዱም፤ እኔ​ንም ደግሞ ባር​ኩኝ።”


በእ​ር​ስዋ ሰላም፥ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋ​ልና ወደ እር​ስዋ ላስ​ማ​ረ​ክ​ኋ​ችሁ ሀገር ሰላ​ምን ፈልጉ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልዩ።”


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ቡ​ታል። ካህ​ኑም ሁሉን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ለቍ​ር​ባን ያቀ​ር​በ​ዋል፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos