1 ሳሙኤል 28:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም በሕልም አላሚዎች፥ ወይም በነጋሪዎች፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔር ግን በሕልምም ሆነ በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ጌታን ጠየቀ፤ ጌታ ግን በሕልምም ሆነ በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባው እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔር ግን በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አማካይነት መልስ እንዲሰጠው አልፈቀደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም። |
በፍርዱ ልብሰ እንግድዓም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን ታደርጋለህ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ወደ ቤተ መቅደስ በገባ ጊዜ በአሮን ልብ ላይ ይሆናሉ፤ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ የእስራኤልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸከማል።
የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር።
ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰበሩ፤ ንጉሥዋና አለቃዋ በአሕዛብ መካከል አሉ፤ ሕግም የለም። ነቢያቷም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላዩም።
“ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢትን ይናገራሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፤ ጐልማሶቻችሁም ራእይን ያያሉ፤
ልብሰ እንግድዓውንም በእርሱ ላይ አደረገ፤ በልብሰ እንግድዓውም ላይ የምልክትና የእውነት መገለጫዎችን አኖረበት።
እርሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ለእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራእይ እገለጥለታለሁ፤ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ በቃሉ ይውጡ፤ በቃሉም ይግቡ።”
እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
እኛም እግዚአብሔርን የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እርሱን ይሰማዋል እንጂ ኃጥኣንን እንደማይሰማቸው እናውቃለን።
ስለ ሌዊም እንዲህ አለ፥ ለሌዊ ቃሉን፥ በመከራም ለፈተኑት፥ በክርክር ውኃም ለሰደቡት፥ ለእውነተኛው ሰው ጽድቁን መልስ።
ሳኦልም፥ “ልውረድና ፍልስጥኤማውያንን ልከተልን? በእስራኤልስ እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀው። በዚያ ቀን ግን እግዚአብሔር አልመለሰለትም።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ለምን አወክኸኝ? ለምንስ አስነሣኸኝ?” አለው። ሳኦልም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ይወጉኛልና እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቆአል፤ በነቢያት ወይም በሕልም አላሚዎች አልመለሰልኝም፤ ስለዚህም የማደርገውን ታስታውቀኝ ዘንድ ጠራሁህ” አለው።