የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊም እንዲህ አሉአቸው፥ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም፤ ይህ ነውር ይሆንብናልና።
1 ሳሙኤል 11:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሞናዊው ናዖስም፦“ ቀኝ ዐይናችሁን ብታወጡ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብን አደርጋለሁ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሞናዊው ናዖስ፣ “ከእናንተ ጋራ ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሞናዊው ናዖስ ግን፥ “ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የማደርገው የእያንዳንዳችሁን ቀኝ ዐይን አውጥቼ እስራኤልን ሁሉ ካዋረድሁ በኋላ ብቻ ነው” ሲል መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖስም “ከእናንተ ጋር የውል ስምምነት ማድረግ የምችልበት አንድ ዐይነት ግዴታ አለ፤ ይኸውም የእያንዳንዱን ሰው ቀኝ ዐይን በማውጣት በእስራኤላውያን ላይ አሳፋሪ ውርደት አመጣለሁ” ሲል መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሞናዊውም ናዖስ፦ ቀኝ ዓይናችሁን ሁሉ በማውጣት ቃል ኪዳን አደርግላችኋለሁ፥ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብ አደረጋለሁ አላቸው። |
የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊም እንዲህ አሉአቸው፥ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም፤ ይህ ነውር ይሆንብናልና።
ሕዝቅያስንም አትስሙ፤ የአሶር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ጋር ታረቁ፤ ወደ እኔም ውጡ፤ እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፤ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ፤
ደግሞም፥ “እኔ የአባቶችህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን መለሰ።
አንተ አለቃ ነህን? ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አገባኸንን? እርሻንና የወይን ቦታንስ አወረስኸንን? የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም” አሉ።
ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዐይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አውርደው በእግር ብረት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።
የአሞንም ልጆች ንጉሥ ናዖስ እንደ መጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሳለ፦ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን አላችሁኝ።
ዳዊትም በአጠገቡ ለቆሙት ሰዎች፦ ይህን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድል፥ ከእስራኤልም ተግዳሮትን ለሚያርቅ ሰው በውኑ ይህ ይደረግለታል? የሕያው አምላክን ጭፍሮች የሚገዳደር ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ነው?” ብሎ ተናገራቸው።