1 ሳሙኤል 1:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐና ግን ከእርሱ ጋር አልወጣችም። ለባልዋም፥ “ሕፃኑን ጡት እስከ አስጥለው፥ ከእኔም ጋር እስኪወጣና በእግዚአብሔር ፊት እስኪታይ ድረስ አልወጣም፤ በዚያም ለዘለዓለም ይኖራል” ብላዋለችና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐና ግን አልሄደችም፤ እርሷም ባሏን፣ “ሕፃኑ ጡት ከተወ በኋላ፣ ወስጄ በእግዚአብሔር ፊት አቀርበዋለሁ፤ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም በዚያ ይኖራል” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐና ግን አልሄደችም፤ ምክንያቱም ለባሏ፥ “ሕፃኑ ጡት እንደተወ፥ በጌታ ፊት ቀርቦ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜም በዚያ እንዲኖር፥ አመጣዋለሁ” ብላው ነበርና ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ልጄ ጡት በሚተውበት ጊዜ እስከ ሕይወቱ ፍጻሜ ወደሚኖርበት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወዲያውኑ እወስደዋለሁ” ብላ ለባልዋ ነግራው ስለ ነበር ሐና በዚህ ጊዜ አብራ አልወጣችም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐና ግን አልወጣችም፥ ባልዋንም፦ ሕፃኑ ጡት እስኪተው ድረስ እቀመጣለሁ፥ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ ዘንድ፥ በዚያም ለዘላለም ይሆን ዘንድ አመጣዋለሁ አለችው። |
ጌታው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ፈራጆች ይውሰደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃኑም አቅርቦ አፍንጫውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ባሪያው ይሁነው።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤
አንተ በምድር ሁሉ ጌታ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ስንሻገር የዮርዳኖስ ወንዝ ስለ ደረቀ ነው፤ እነዚህ ድንጋዮችም ለእስራኤል ልጆች ለዘለዓለም መታሰቢያ ይሆናሉ።”
እርስዋም፥ “አዶናይ፥ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! የባርያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለባርያህም ወንድ ልጅ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለአንተ እሰጠዋለሁ፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥም አይጠጣም። ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም” ብላ ስእለት ተሳለች።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “በድለኻል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዙን አልጠበቅህምና፤ ዛሬ እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘለዓለም አጽንቶልህ ነበር።
በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ተዉት። እነርሱም ወደ አርማቴም ወደ ቤታቸው ገቡ፤ ልጁም በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
ዳዊትም አንኩስን፥ “አሁን አገልጋይህ የሚያደርገውን ንገረው” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “እንግዲህ በዘመኑ ሁሉ ራሴን ጠባቂ አደርግሃለሁ” አለው።
ብላቴናው ሳሙኤልም በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያም ዘመን የእግዚአብሔር ቃል ክቡር ነበረ፤ ራእይም አይገለጥም ነበር።