እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
1 ጴጥሮስ 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ይመለከታሉ፤ ጆሮዎቹም ጸሎታቸውን ለመስማት ተከፍተዋል፤ በክፉ አድራጊዎች ላይ ግን ጌታ የቊጣ ፊቱን ያሳያል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸውና፥ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል፥ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው። |
እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። አሁንም ባለማወቅህ በድለሃል፤ ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል።”
እግዚአብሔር ከኃጥኣን ፈጽሞ ይርቃል፤ የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል። ከዐመፃ ጋር ካለ ብዙ ሀብት ይልቅ፥ ከእውነት ጋር ያለ ጥቂት ሀብት ይሻላል። አካሄዱ ከእግዚአብሔር ይቃናለት ዘንድ፥ የደግ ሰው ልብ እውነትን ያስባል።
ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።”
ፊቴንም በእነርሱ ላይ አጸናለሁ፤ ከእሳትም አይወጡም፤ እሳትም ይበላቸዋል፤ ፊቴንም በእነርሱ ላይ በአጸናሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
“ከእስራኤልም ልጆች፥ ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ያንም ሰው ከሕዝቡ ለይች አጠፋዋለሁ።
መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የቅዱሳኔንም ስም ያጐስቍል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ።
“እነርሱን ተከትሎ ያመነዝር ዘንድ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን የሚከተል ሰው ቢኖር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ።
ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሏችሁም ያሸንፉአችኋል። ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።
የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? እነዚህ ሰባቱ ደስ ብሎአቸው በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ያያሉ፣ እነዚህም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የእግዚአብሔር ዓይኖች ናቸው።
እኛም እግዚአብሔርን የሚፈራውንና ፈቃዱን የሚያደርገውን እርሱን ይሰማዋል እንጂ ኃጥኣንን እንደማይሰማቸው እናውቃለን።
አምላክህ እግዚአብሔር የሚጐበኛት ሀገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእርስዋ ላይ ነው።