የቤቱንም ውስጥ በተጐበጐበና በፈነዳ አበባ፥ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር።
1 ነገሥት 6:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ፥ የፈነዳም አበባ ሥዕል ቀረጸባቸው፤ በተቀረጸውም ሥራ ላይ በወርቅ ለበጣቸው፤ እስከ መድረካቸውም የተያያዙ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችንም ቀረጸባቸው፤ ቅርጹን ሠራ፤ ጥሩ አድርጎም በወርቅ ለበጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱንም ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፤ በተቀረጸውም ሥራ ላይ በወርቅ ለበጣቸው። |
የቤቱንም ውስጥ በተጐበጐበና በፈነዳ አበባ፥ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር።
ሁለቱንም ደጆች ከጥድ እንጨት ሠራ፤ አንዱ ደጅ በማጠፊያ ከተያያዙ ከሁለት ሣንቃዎች ተሠራ፤ ሁለተኛውም ደጅ በማጠፊያ ከተያያዙ ከሁለት ሣንቃዎች ተሠራ።
የውስጠኛውንም አደባባይ ቅጥር ሦስቱን ተራ በተጠረበ ድንጋይ፥ አንዱንም ተራ በዝግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመቅደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለልም መጋረጃ ሠራ።
ውፍረቱም አንድ ጋት ነበረ። ከንፈሩም እንደ ጽዋ ከንፈር ተሠርቶ ነበር፤ እንደ ሱፍ አበባዎች ሆኖ ተከርክሞ ነበር። ሁለት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ይይዝ ነበር።
በክፈፎቻቸውም ኪሩቤልና አንበሶች የዘንባባ ዛፎችም ነበሩ፤ እያንዳንዱም ፊት ለፊት በስተውስጥና በዙሪያው ተያይዞ ነበር።
የመብራቶች መቅረዞችንና በላያቸው ያሉ መብራቶችን፥ ጽዋዎቹን፥ ማንኪያዎቹን፥ ሥራ የሚሠሩባቸው ጻሕሎችንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።
ውስጠኛው የእግዚአብሔር ቤት ደጅና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ የሚወስደው የውስጠኛውም የቤተ መቅደሱ ደጆች የወርቅ ነበሩ። እንዲሁም ሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ።
በዕቃ ቤቶቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ የዐይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩባቸው፤ ደግሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
መስኮቶቹም፥ መዛነቢያዎቹም፥ የዘንባባ ዛፎቹም ወደ ምሥራቅ እንደሚመለከተው በር ልክ ነበሩ፤ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ መዛነቢያዎቹም በፊቱ ነበሩ።
ኪሩቤልና የዘንባባው ዛፎች ተቀርጸውበት ነበር፤ የዘንባባውም ዛፍ ከኪሩብና ከኪሩብ መካከል ነበረ፤ ለእያንዳዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበረው።