Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 6:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እነርሱንም ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ኪሩቤልን፣ የዘንባባ ዛፎችንና የፈኩ አበቦችንም ቀረጸባቸው፤ ቅርጹን ሠራ፤ ጥሩ አድርጎም በወርቅ ለበጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እነርሱንም ሙሉ በሙሉ በወርቅ በተለበጡ በኪሩቤል፥ በዘንባባ ዛፎችና በፈኩ የአበባ ቅርጾች አስጌጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በተ​ቀ​ረ​ጸ​ውም ሥራ ላይ በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው፤ እስከ መድ​ረ​ካ​ቸ​ውም የተ​ያ​ያዙ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፤ በተቀረጸውም ሥራ ላይ በወርቅ ለበጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 6:35
11 Referencias Cruzadas  

የሊባኖስ ዛፍ እንጨት ሳንቃዎች በአበባ እንቡጦችና በፈኩ አበባዎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ውስጡም ሁሉ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት ተጠርቦ በተሠራ ሳንቃ ስለ ተለበደ የግንቡ ድንጋዮች አይታዩም ነበር።


ሁለቱንም በሮች ከዝግባ እንጨት ሠራ፤ አንዱ በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፤ ሁለተኛውም በር በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ።


በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አንድ የውስጥ አደባባይ ሠራ፤ በዚህም አደባባይ ዙሪያ በየሦስቱ ዙር የድንጋይ ረድፍ አንድ የሊባኖስ ዛፍ ሠረገላ ሳንቃ የተጋደመበት ግንብ አደረገ።


የገንዳው ጐኖች ውፍረት አንድ መዳፍ ነበር፤ የጽዋ ቅርጽ ያለው አበባ የሚመስል የአፉ ክፈፍ የአሸንድዬ አበባ ቅርጽ ነበረው፤ ይህም ገንዳ አርባ ሺህ ሊትር ያኽል ውሃ የሚይዝ ነበር።


በእነዚሁ መደገፊያዎችና ጠፍጣፋ ነሐሶች መካከል ባለው ክፍት ቦታ ሁሉ በኪሩቤል፥ በአንበሶችና በዘንባባ ዛፎች አምሳል በተሠሩ ቅርጾች አጊጠው ነበር፤ እንዲሁም ዙሪያቸው የአበባ ጒንጒን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር።


የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጌጦች፥ ቀንዲሎችና መኰስተሪያዎች፥


የመብራት ማብሪያና ማጥፊያዎች፥ ማንቈርቈሪያዎች፥ ጥናዎችና የእሳት መጫሪያዎች፤ እነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ናቸው፤ የቤተ መቅደሱ የውጪ በሮችና የቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ።


የግድግዳዎችዋን ጌጣ ጌጦች በመጥረቢያና በመዶሻ ሰባበሩ።


ማረፊያ ክፍሎቹና ዐምዶቻቸው በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶችና ዐይነ ርግቦች ነበሩአቸው፤ በስተመጨረሻ ያሉትም ክፍሎች በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩአቸው፤ በግድግዳ ዐምዶቻቸውም ላይ የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩባቸው።


በስተ መጨረሻ ያለው ክፍል መስኮቶቹና የተሳሉት የዘንባባ ዛፍ ቅርጾችም ከዚህ በፊት በምሥራቁ የቅጽር በር ከታዩት ጋር ተመሳሳይ መጠን ነበራቸው፤ ወደ እርሱም የሚያመሩ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ በውስጥ መተላለፊያ በስተመጨረሻ ያለው ክፍልም በአደባባዩ ትይዩ ይገኝ ነበር።


በመለበጃውም ላይ ያለው ቅርጽ የዘንባባ ዛፎችና የኪሩቤል ስዕል ነበር፤ በክፍሉም ዙሪያ የዘንባባና የኪሩቤል ሥዕሎች ተሰባጥረው ተስለውበታል፤ እያንዳንዱም ኪሩብ ሁለት ፊቶች ነበሩት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos