Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 40:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ክፍሎቹ እንደ መተላለፊያ በረንዳዎቹ ከግራና ከቀኝ በኩል ትንንሽ መስኮቶች አሏቸው። በዙሪያው ያሉ መስኮቶች በመግቢያው በር ፊት ለፊት የነበሩ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ ክፍል ግራና ቀኝ ግድግዳ ላይ ደግሞ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾበታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ ትናንሽ መስኮቶች ነበሩአቸው፤ ደግሞም በመተላለፊያው ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ማረፊያ ክፍሎቹና ዐምዶቻቸው በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶችና ዐይነ ርግቦች ነበሩአቸው፤ በስተመጨረሻ ያሉትም ክፍሎች በውስጥ በኩል ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩአቸው፤ በግድግዳ ዐምዶቻቸውም ላይ የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ነበሩባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በዘበኛ ጓዳዎቹም በበሩ ውስጥ በዙሪያው በነበሩትም በግንቡ አዕማድ የዓይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩባቸው፥ ደግሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙሪያው መስኮቶች ነበሩ፥ በግንቡም አዕማድ ሁሉ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 40:16
29 Referencias Cruzadas  

በቤ​ቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በው​ስ​ጥና በውጭ የኪ​ሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረጸ።


ሁለ​ቱ​ንም ሣን​ቃ​ዎች ከወ​ይራ እን​ጨት ሠራ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባ​ባ​ውን ዛፍ በወ​ርቅ ለበጠ።


የኪ​ሩ​ቤ​ል​ንና የዘ​ን​ባባ ዛፍ፥ የፈ​ነ​ዳም አበባ ሥዕል ቀረ​ጸ​ባ​ቸው፤ በተ​ቀ​ረ​ጸ​ውም ሥራ ላይ በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው፤ እስከ መድ​ረ​ካ​ቸ​ውም የተ​ያ​ያዙ ነበሩ።


ለቤ​ቱም በዐ​ይነ ርግብ የተ​ዘጉ መስ​ኮ​ቶ​ችን አደ​ረገ።


መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ነበሩ፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም በሦ​ስት ወገን ፊት ለፊት ይተ​ያዩ ነበር።


ታላ​ቁ​ንም ቤት በዝ​ግባ እን​ጨት ከደ​ነው፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው፤ የዘ​ን​ባ​ባና የሰ​ን​ሰ​ለት አም​ሳ​ልም ቀረ​ጸ​በት።


በዕቃ ቤቱም ፊት በዚህ በኩል አንድ ክንድ፥ በዚ​ያም በኩል አንድ ክንድ የሆነ ዳርቻ ነበረ፤ የዕቃ ቤቱም በዚህ በኩል ስድ​ስት ክንድ በዚ​ያም በኩል ስድ​ስት ክንድ ነበሩ።


ከበ​ሩም መግ​ቢያ ፊት ጀምሮ እስከ ውስ​ጠ​ኛው የበሩ ደጀ ሰላም መጨ​ረሻ ድረስ አምሳ ክንድ ነበረ።


በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ እንደ እነ​ዚያ መስ​ኮ​ቶች የሚ​መ​ስሉ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ሰባት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ፤ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በፊቱ ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ አንዱ በዚህ አን​ዱም በዚያ ወገን ሆኖ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።


እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መቱ አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


በዙ​ሪ​ያ​ውም ደጀ ሰላ​ሞች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ታ​ቸ​ውም ሃያ አም​ስት ክንድ፥ ወር​ዳ​ቸ​ውም አም​ስት ክንድ ነበረ።


መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበሩ።


እን​ደ​ዚ​ያም መጠን የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በእ​ር​ሱና በመ​ዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም ዙሪያ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹም በስተ ውጭ ወደ አለው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ደ​ርሱ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።


የዕቃ ቤቶ​ቹ​ንና የግ​ን​ቡን አዕ​ማድ፥ መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ለካ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​በት፤ ርዝ​መ​ቱም አምሳ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ አም​ስት ክንድ ነበረ።


የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ወጡ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።


የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝ​መት አንድ ዘንግ፤ ወር​ዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም ደጀ ሰላም፤ በስ​ተ​ው​ስጥ በኩል የሚ​ገኝ የበሩ የመ​ድ​ረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።


ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባ​ባው ዛፎች ተቀ​ር​ጸ​ው​በት ነበር፤ የዘ​ን​ባ​ባ​ውም ዛፍ ከኪ​ሩ​ብና ከኪ​ሩብ መካ​ከል ነበረ፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበ​ረው።


በግ​ን​ቡም ላይ በተ​ቀ​ረ​ጹት ዓይ​ነት በእ​ነ​ዚህ በመ​ቅ​ደሱ መዝ​ጊ​ያ​ዎች ላይ ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፎች ተቀ​ር​ጸው ነበር፤ በስ​ተ​ው​ጭም በአ​ለው በደጀ ሰላሙ ፊት የእ​ን​ጨት መድ​ረክ ነበረ።


በደጀ ሰላ​ሙም በሁ​ለቱ ወገን በዚ​ህና በዚያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶ​ችና የተ​ቀ​ረጹ የዘ​ን​ባባ ዛፎች ነበ​ሩ​በት፤ የመ​ቅ​ደ​ሱም ጓዳ​ዎ​ችና የእ​ን​ጨቱ መድ​ረክ እን​ዲሁ ነበሩ።


ወደ ውስ​ጥም ገባ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ው​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ወርድ ስድ​ስት ክንድ ነበረ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ።


በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሃ​ያው ክንድ አን​ጻር፥ በው​ጭ​ውም አደ​ባ​ባይ በወ​ለሉ አን​ጻር በሦ​ስት ደርብ በት​ይዩ የተ​ሠራ መተ​ላ​ለ​ፊያ ነበረ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በበ​ጎች በር አጠ​ገብ መጠ​መ​ቂያ ነበ​ረች፤ ስም​ዋ​ንም በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉ​አ​ታል፤ አም​ስት እር​ከ​ኖ​ችም ነበ​ሩ​አት።


አሁን ግን ታወ​ቀኝ፤ በግ​ል​ጥም ተረ​ዳኝ፤ በመ​ስ​ታ​ወ​ትም እን​ደ​ሚ​ያይ ሰው ዛሬ በድ​ን​ግ​ዝ​ግ​ዝታ እና​ያ​ለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እና​ያ​ለን፤ አሁን በከ​ፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልኝ መጠን ሁሉን አው​ቃ​ለሁ።


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos