ንጉሡም ተማከረ፤ ሁለትም የወርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስራኤል ሆይ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት ይበቃችኋል፤ ከግብፅ ምድር ያወጡአችሁ አማልክቶቻችሁ እነሆ” አላቸው።
1 ነገሥት 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአንተም አስቀድመው ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስቈጣኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎችን አማልክትና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች አደረግህ፤ ወደ ኋላህም ተውኸኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንተ በፊት ከነበሩት ሁሉ ይልቅ አንተ የከፋ ሥራ ሠራህ፤ ለራስህም ከቀለጠ ብረት ሌሎች አማልክትን ሠራህ፤ ቍጣዬን አነሣሣህ፤ ወደ ኋላህም ጣልኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችና ከብረት የተቀረጹ ምስሎችን ለማምለክ በመሥራትህ ቁጣዬን አነሣሥተሃል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችና ከብረት የተቀረጹ ምስሎችን ለማምለክ በመሥራትህ ቊጣዬን አነሣሥተሃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአንተም አስቀድመው ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስቆጣኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎችን አማልክትና ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎች አደረግህ፤ ወደ ኋላህም ጣልኸኝ። |
ንጉሡም ተማከረ፤ ሁለትም የወርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስራኤል ሆይ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት ይበቃችኋል፤ ከግብፅ ምድር ያወጡአችሁ አማልክቶቻችሁ እነሆ” አላቸው።
ሮብዓምም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሠራ፤ አባቶቹ በሠሩት ኀጢአትና በደል ሁሉ እንደ አስቀኑት በሠራው ኀጢአት አስቀናው።
ከነገሠም በኋላ የኢዮርብዓምን ወገን ሁሉ አጠፋ፥ በባሪያው በሴሎናዊው በአኪያ እጅ እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ እስኪያጠፋው ድረስ ከኢዮርብዓም ወገን ሕይወት ያለውን አላስቀረም።
ይኸውም ኢዮርብዓም ስለ ሠራው ኀጢአት፥ እስራኤልንም ስላሳተበት፥ የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን ስላስቈጣበት ማስቈጣት ነው።
በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፥ በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም መንገድ እስራኤልንም ባሳተበት ኀጢአት ሄደ።
በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ አልበቃውም፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤያትባሔልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በዓልን አመለከ ሰገደለትም።
አክዓብም የማምለኪያ ዐፀድን አሠራ፤ አክዓብም ሰውነቱ እንድትጠፋ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይልቅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያስቈጣውን ነገር አበዛ።
አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለበዓል መሠዊያን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ አመለካቸውም።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ። መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገርን አደረገ።
ምሽጎቹንም ከተሞች፥ መልካምን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጕድጓዶች፥ የወይኖቹንና የወይራዎቹን ቦታዎች፥ ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፤ በሉም፤ ጠገቡም፤ ወፈሩም፤ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው።
“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕረትን ታደርጋለህ፤ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ።
ያስቈጡኝ ዘንድ፥ ለሰማይ ንግሥት እንጎቻ እንዲያደርጉ፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፤ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፤ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ።
ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ከአደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዘንግተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ኀጢአትሽን ተሸከሚ።”
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን አይተሃልን? በዚህ የሚያደርጉትን ይህን ኀጢአት ያደርጉ ዘንድ ለይሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድሪቱን በኀጢአት ሞልተዋታል፤ ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፤ እነሆም ቅርንጫፉን አስረዝመዋል። ይዘባበታሉም።
እጅ መሳይንም ዘረጋ፤ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ ቅንአት የተባለው ምስል ወደ አለበት አመጣኝ፤
ጣዖታትንም አትከተሉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የአማልክት ምስሎች ለእናንተ አታድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በጣዖቶቻቸውም አስቈጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ።