La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሥጋ​ውን ጎድቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን ነፍሱ ትድን ዘንድ እን​ዲህ ያለ​ውን ሰው ለሰ​ይ​ጣን አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሥጋው ጠፍቶ መንፈሱ በጌታ ቀን ትድን ዘንድ፣ እንደዚህ ዐይነቱ ለሰይጣን ይሰጥ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንደዚህ ያለው ሰው፥ መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን እንድትድን፥ ሥጋው ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ስጡት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በኃጢአት የተሞላው የዚህ ሰው ሥጋ ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል። ይህንንም የምታደርጉት ጌታ ኢየሱስ ለፍርድ በሚመጣበት ቀን የዚህ ሰው ነፍስ እንድትድን ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 5:5
23 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰይ​ጣ​ንን አለው፥ “እነሆ፥ ሥጋ​ው​ንና አጥ​ን​ቱን በእ​ጅህ ሰጠ​ሁህ። ነገር ግን ሕይ​ወ​ቱን ተው።”


በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይፈ​ር​ዳል፥ ሬሳ​ዎ​ች​ንም ያበ​ዛል፤ በም​ድር ላይ የብ​ዙ​ዎ​ችን ራሶች ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል።


አንተ በበትር ትመታቸዋለህ፥ ነፍሳቸውን ግን ከሞት ታድናለህ።


ካህ​ኑም ቢያ​የው፥ ነጭም ጠጕር ባይ​ኖ​ር​በት፥ ወደ ቆዳ​ውም ውስጥ ባይ​ጠ​ልቅ ነገር ግን ቢከ​ስም፥ ካህኑ ሰባት ቀን ይለ​የ​ዋል።


ያን ጊዜ ኢየሱስ “ሂድ፤ አንተ ሰይጣን ‘ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ’ ተብሎ ተጽፎአልና” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ስም​ዖን፥ ስም​ዖን ሆይ፥ ሰይ​ጣን እንደ አጃ ሊያ​በ​ጥ​ራ​ችሁ አሁን ልመ​ናን ለመነ።


ይኸ​ውም ዐይ​ና​ቸ​ውን ትከ​ፍ​ት​ላ​ቸው ዘንድ፥ ከጨ​ለ​ማም ወደ ብር​ሃን፥ ሰይ​ጣ​ንን ከማ​ም​ለ​ክም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ል​ሳ​ቸው ዘንድ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በስ​ሜም በማ​መን ከቅ​ዱ​ሳን ጋር አን​ድ​ነ​ትን ያገኙ ዘንድ ነው።’


እር​ሱም በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ቀን ያለ ነውር ትገኙ ዘንድ እስከ ፍጻሜ ያጸ​ና​ች​ኋል።


ነገር ግን በተ​ፈ​ረ​ደ​ብን ጊዜ ከዓ​ለም ጋር እን​ዳ​ን​ኰ​ነን በጌታ እን​ገ​ሠ​ጻ​ለን።


በውጭ ያሉ​ትን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ይቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም፤ ክፉ​ውን ከእ​ና​ንተ አርቁ።


እና​ንተ ትእ​ዛ​ዝን በፈ​ጸ​ማ​ችሁ ጊዜ የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን ሁሉ እኛ ልን​በ​ቀ​ለው ዝግ​ጁ​ዎች ነን።


ስለ​ዚ​ህም ቢሆን በብዙ ራእይ እን​ዳ​ል​ታ​በይ ሰው​ነ​ቴን የሚ​ወጋ እር​ሱም የሚ​ጐ​ስ​መኝ የሰ​ይ​ጣን መል​እ​ክ​ተኛ ተሰ​ጠኝ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።


እርሱ የጀ​መ​ረ​ላ​ች​ሁን በጎ​ውን ሥራ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ እስ​ከ​ሚ​መ​ጣ​በት ቀን ድረስ እርሱ እን​ደ​ሚ​ፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ አም​ና​ለሁ።


ከእነዚያም እንዳይሳደቡ ይማሩ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው ሄሜኔዎስና እስክንድሮስ ናቸው።


በዚያን ቀን ከጌታ ምሕረትን እንዲያገኝ ጌታ ይስጠው፤ በኤፌሶንም እንዴት እንዳገለገለኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ።


ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።