1 ዜና መዋዕል 27:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ከፋሬስ ልጆች ነበረ፤ ለመጀመሪያው ወር በጭፍራ አለቆች ሁሉ ላይ ተሾሞ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ከፋሬስ ልጆች ነበረ፤ ለመጀመሪያ ወር በሠራዊቱ አለቆች ሁሉ ላይ ተሾሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ከፋሬስ ልጆች ነበረ፤ ለመጀመሪያ ወር በጭፍራ አለቆች ሁሉ ላይ ተሹሞ ነበር። |
ለመጀመሪያው ወር በአንደኛው ክፍል ላይ የዘብድኤል ልጅ ያሶብአም ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
በሁለተኛውም ወር ክፍል ላይ የኤቲ ልጅ ዶድያ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሚኮሎት አለቃ ነበር፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
በመጀመሪያም የይሁዳ ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን አለቃ ነበረ።