Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን መባ​ውን ያቀ​ረበ ከይ​ሁዳ ነገድ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በመጀመሪያው ቀን ስጦታውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በመጀመሪያውም ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በመጀመሪያው ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በመጀመሪያውም ቀን መባውን ያቀረበ ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 7:12
13 Referencias Cruzadas  

የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤


የልያ ልጆች፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስም​ዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳ​ኮር፥ ዛብ​ሎን፤


መን​ግ​ሥት ከይ​ሁዳ አይ​ጠ​ፋም፤ ምስ​ፍ​ናም ከአ​ብ​ራኩ፥ ለእ​ርሱ የሚ​ጠ​ብ​ቀ​ውን እስ​ኪ​ያ​ገኝ ድረስ፤ የአ​ሕ​ዛብ ተስ​ፋ​ቸው እርሱ ነውና፤


“ይሁዳ፥ ወን​ድ​ሞ​ችህ አን​ተን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ እጅህ በጠ​ላ​ቶ​ችህ ደን​ደስ ላይ ነው፤ የአ​ባ​ትህ ልጆች በፊ​ትህ ይሰ​ግ​ዳሉ።


ከእ​ና​ን​ተም ጋር የሚ​ቆ​ሙት ሰዎች ስሞ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ከሮ​ቤል የሰ​ዲ​ዮር ልጅ ኤሊ​ሱር፥


ከይ​ሁዳ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን፥


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም የይ​ሁዳ ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን አለቃ ነበረ።


በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ በየ​ቀኑ መሠ​ዊ​ያ​ውን ለመ​ቀ​ደስ እያ​ን​ዳ​ንዱ አለቃ መባ​ውን በቀን በቀኑ ያቅ​ርብ” አለው።


መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤


ኤስሮምም አራምን ወለደ፤ አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤


የዕ​ሤይ ልጅ፥ የኢ​ዮ​ቤድ ልጅ፥ የቦ​ዔዝ ልጅ፥ የሰ​ል​ሞን ልጅ፥ የነ​ዓ​ሶን ልጅ፥


አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፥ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos