የአሞን ልጆች አለቆች ግን ሐናንን፥ “ዳዊት የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ አባትህን በማክበር ነውን? አገልጋዮቹስ ከተማዪቱን ለመመርመርና ሀገሪቱንም ለመሰለል ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?” አሉት።
1 ዜና መዋዕል 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐናንም የዳዊትን አገልጋዮች ወስዶ የጢማቸውን ግማሽ አስላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ለሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ ላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ መቀመጫቸው ድረስ መኻል ለመኻል ቀዶ ሰደዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐኖንም የዳዊትን ባርያዎች ወስዶ አስላጫቸው፥ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሐኑን የዳዊትን መልእክተኞች ይዞ ጢማቸውን ላጨ፤ ኀፍረተ ሥጋቸው እስኪታይ ድረስ ከወገባቸው በታች ያለውን ልብስ ቈረጠና ወደ አገራቸው ሰደዳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐኖንም የዳዊትን ባሪያዎች ወስዶ አስላጫቸው፤ ልብሳቸውንም እስከ ወገባቸው ድረስ ከሁለት ቀድዶ ሰደዳቸው። |
የአሞን ልጆች አለቆች ግን ሐናንን፥ “ዳዊት የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ አባትህን በማክበር ነውን? አገልጋዮቹስ ከተማዪቱን ለመመርመርና ሀገሪቱንም ለመሰለል ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?” አሉት።
ሰዎችም ሄደው በሰዎቹ ላይ የተደረገውን ለዳዊት አስታወቁት። ሰዎቹም በብዙ አፍረዋልና ይቀበሏቸው ዘንድ ሰዎችን ላኩ፤ ንጉሡም፥ “ጢማችሁ እስኪያድግ ድረስ በኢያሪኮ ተቀመጡ፥ ከዚያም በኋላ ተመለሱ” አለ።
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብፅንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ፥ ገላቸውንም ገልጦ ለግብፅ ኀፍረት ይነዳቸዋል።
ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውንም ቀድደው እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው የያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ፥ ከሰማርያም መጡ።
በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃነት አለ፤ ጽሕማቸውን ሁሉ ይላጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ሁሉም በወገባቸው ማቅን ይታጠቃሉ።