ኢያሱ 19:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራቸውም የሚከተሉትን ያካትታል፤ ኢይዝራኤል፣ ከስሎት፣ ሱነም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበራቸውም የሚያጠቃልለው ኢይዝራኤልን፥ ከስሎትን፥ ሱነምን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድሩም ክልል ኢይዝራኤልን፥ ከሱሎትን፥ ሹኔምን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንበራቸውም ኢይዝራኤል፥ ከልሰሉት፥ ሱሳን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንበራቸውም ወደ ኢይዝራኤል፥ |
ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ የወይን ተክል ቦታ ላይ አንድ ነገር ደረሰ፤ ቦታውም በኢይዝራኤል ውስጥ ከሰማርያ ንጉሥ ከአክዓብ ቤተ መንግሥት አጠገብ ነበር።
አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደ ሱነም ሄደ። በዚያም አንዲት ሀብታም ሴት ነበረች፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ አጥብቃ ለመነችው፤ በዚያም ባለፈ ቍጥር ምግብ ለመብላት ወደ ቤቷ ይገባ ነበር።
ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም፣ ከአዛሄል ጋራ ራማት ላይ ባደረገው ጦርነት ሶርያውያን ካቈሰሉት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። ከዚያም የአክዓብ ልጅ ኢዮራም ስለ ታመመ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራሆም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።
ንጉሥ ኢዮራም ግን የሶርያን ንጉሥ አዛሄልን ጦርነት በገጠመው ጊዜ፣ ሶርያውያን ካደረሱበት ቍስል ለማገገም ወደ ኢይዝራኤል ተመልሶ ነበር። ኢዩም፣ “እንግዲህ ሐሳባችሁ እንዲህ ከሆነ፣ ይህን ነገር ወደ ኢይዝራኤል ሄዶ እንዳይናገር፣ ማንም ሰው ከዚህች ከተማ ሾልኮ እንዳይወጣ ጠብቁ” አለ።
የዮሴፍም ዘሮች፣ “ኰረብታማው አገር አይበቃንም፤ ደግሞም በሜዳው ላይ ያሉት በቤትሳንና በሰፈሮቿ፣ እንዲሁም በኢይዝራኤል ሸለቆ የሚኖሩት ከነዓናውያን ሁሉ የብረት ሠረገሎች አሏቸው” አሉት።