አክዓብም ናቡቴን፣ “የወይን ተክል ቦታህ ከቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ፣ የአትክልት ቦታ እንዳደርገው ልቀቅልኝ፤ በምትኩ ከዚህ የበለጠ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ የተሻለ ሆኖ ከታየህም የሚያወጣውን ገንዘብ እከፍልሃለሁ” አለው።
2 ነገሥት 9:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ይህን ሲያይ፣ ወደ ቤት ሀጋን በሚያወጣው መንገድ ሸሸ፤ ኢዩም እያሳደደ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እርሱንም ግደሉት!” አለ። እነርሱም በይብለዓም ከተማ አጠገብ በጉር ዐቀበት መንገድ ላይ በሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቈሰሉት፤ እርሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሽቶ፤ እዚያው ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ አካዝያስ የሆነውን ነገር ሁሉ በተመለከተ ጊዜ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ቤትሀጋን ከተማ ሸሽቶ ሄደ፤ ኢዩ ተከታትሎ እያሳደደው “እርሱንም ግደሉት!” ሲል ለወታደሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አካዝያስን ተከታትለው በዪብለዓም ከተማ አጠገብ በምትገኘው በጉር የአቀበት መንገድ ላይ በሠረገላው ሲበር መትተው አቆሰሉት፤ እርሱ ግን እንደ ምንም ጨክኖ መጊዶ ከተማ እስኪደርስ ተጓዘ፤ በዚያም ሞተ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ አካዝያስ የሆነውን ነገር ሁሉ በተመለከተ ጊዜ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ቤትሀጋን ከተማ ሸሽቶ ሄደ፤ ኢዩ ተከታትሎ እያሳደደው “እርሱንም ግደሉት!” ሲል ለወታደሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አካዝያስን ተከታትለው በዪብለዓም ከተማ አጠገብ በምትገኘው በጉር የአቀበት መንገድ ላይ በሠረገላው ሲበር መትተው አቈሰሉት፤ እርሱ ግን እንደምንም ጨክኖ መጊዶ ከተማ እስኪደርስ ተጓዘ፤ በዚያም ሞተ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ ያን ባየ ጊዜ በአትክልት ቤት መንገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እርሱንም ደግሞ አልተወውም” ብሎ ተከተለው። በይብላሄምም አቅራቢያ ባለችው በጋይ አቀበት በሰረገላው ላይ ወጋው። ወደ መጊዶም ሸሸ፥ በዚያም ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ያንን ባየ ጊዜ በአትክልት ቤት መንገድ ሸሸ። ኢዩም “ይህን ደግሞ በሠረገላው ላይ ውጉት፤” እያለ ተከተለው፤ በይብለዓምም አቅራቢያ ባለችው በጉር ዐቀበት ላይ ወጉት። ወደ መጊዶም ሸሸ፤ በዚያም ሞተ። |
አክዓብም ናቡቴን፣ “የወይን ተክል ቦታህ ከቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ፣ የአትክልት ቦታ እንዳደርገው ልቀቅልኝ፤ በምትኩ ከዚህ የበለጠ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ የተሻለ ሆኖ ከታየህም የሚያወጣውን ገንዘብ እከፍልሃለሁ” አለው።
የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክና በመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎ ቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለው በቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምን ተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣
ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አርባ ዓመት ገዛ። እናቱ ሳብያ የተባለች የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ ነበረች።
ገዳዮቹ ሹማምትም የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ነበሩ። እርሱም ሞተ፤ እንደ አባቶቹም ሁሉ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ አሜስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም፣ ከአዛሄል ጋራ ራማት ላይ ባደረገው ጦርነት ሶርያውያን ካቈሰሉት ቍስል ለመዳን ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ። ከዚያም የአክዓብ ልጅ ኢዮራም ስለ ታመመ፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራሆም ልጅ አካዝያስ ሊጠይቀው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ።
እርሱም፣ “ከእነዚህ ክፉ ሰዎች ድንኳን ራቁ የእነርሱ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትንኩ፤ አለዚያ በእነርሱ ኀጢአት ሁሉ እናንተም ትጠፋላችሁ” ሲል ማኅበሩን አስጠነቀቀ።
እንዲሁም በይሳኮርና በአሴር ውስጥ ቤትሳን፣ ይብለዓም፣ የዶር ሕዝብ፣ ዓይንዶር፣ ታዕናክና መጊዶ በዙሪያቸው ካሉ ሰፈሮቻቸው ጋራ የምናሴ ነበሩ፤ ሦስተኛውም ናፎት ነው።
የምናሴ ነገድ ግን በቤትሳን፣ በታዕናክ፣ በዶር፣ በይብለዓም፣ በመጊዶንና በየአካባቢያቸው ያሉት መንደሮች ነዋሪውን ሕዝብ ስላላስወጡ፣ ከነዓናውያን ኑሯቸውን በዚያው ለማድረግ ወሰኑ።