Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 10:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነርሱ ግን እጅግ ፈርተው ነበርና፣ “ሁለት ነገሥታት ሊቋቋሙት ያልቻሉትን ሰው እኛ እንዴት ልንቋቋመው እንችላለን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከዚህም የተነሣ የሰማርያ ገዢዎች በፍርሃት ተሸብረው፥ “ንጉሥ ኢዮራምና ንጉሥ አካዝያስ ሊቋቋሙ ያልቻሉትን እኛ እንዴት ኢዩን ልንቋቋመው እንችላለን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህም የተነሣ የሰማርያ ገዢዎች በፍርሃት ተሸብረው፥ “ንጉሥ ኢዮራምና ንጉሥ አካዝያስ ሊቋቋሙ ያልቻሉትን እኛ እንዴት ኢዩን ልንቋቋመው እንችላለን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነ​ር​ሱም እጅግ ፈር​ተው፥ “እነሆ፥ ሁለቱ ነገ​ሥ​ታት በፊቱ ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ እኛስ እን​ዴት በፊቱ መቆም እን​ች​ላ​ለን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነርሱ ግን እጅግ ፈርተው “እነሆ፥ ሁለቱ ነገሥታት በፊቱ ይቆሙ ዘንድ አልቻሉም፤ እኛስ እንዴት እንቆማለን?” አሉ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 10:4
8 Referencias Cruzadas  

የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ይህን ሲያይ፣ ወደ ቤት ሀጋን በሚያወጣው መንገድ ሸሸ፤ ኢዩም እያሳደደ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “እርሱንም ግደሉት!” አለ። እነርሱም በይብለዓም ከተማ አጠገብ በጉር ዐቀበት መንገድ ላይ በሠረገላው ውስጥ እንዳለ አቈሰሉት፤ እርሱ ግን ወደ መጊዶ ሸሽቶ፤ እዚያው ሞተ።


ከዚያም ኢዩ ቀስቱን በማስፈንጠር ኢዮራምን በትከሻና ትከሻው መካከል ወጋው፤ ፍላጻውም ዘልቆ ልቡን ስለ ወጋው፣ ሠረገላው ውስጥ ዘፍ ብሎ ወደቀ።


“ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላው ንጉሥ ጋራ ጦርነት ሊገጥም በሚነሣበት ጊዜ፣ ሃያ ሺሕ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን ንጉሥ፣ በዐሥር ሺሕ ሰራዊት መመከት እንደሚችል ተቀምጦ የማይመክር ማን ነው?


ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል።


“አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም በኤዶም ላይ ድንገት እወጣለሁ፤ ከምድሩም አባርረዋለሁ። የመረጥሁትን በርሱ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”


እኔ አልቈጣም። እሾኽና ኵርንችት ምነው በተነሡብኝ! ለውጊያ በወጣሁባቸው፣ አንድ ላይ ባቃጠልኋቸው!


ከጌታችሁ ልጆች መካከል ብልጫ ያለውንና ተገቢ ነው የምትሉትን መርጣችሁ በአባቱ ዙፋን አስቀምጡት። ከዚያም ስለ ጌታችሁ ቤት ተዋጉ።”


እርሱን እስኪ ንካው፣ ግብግቡን ታስታውሳለህ፤ ከቶም አያላምድህም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios