ዘካርያስ 11:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “ብትፈቅዱ ደመወዜን ስጡኝ፤ ባትፈቅዱ ተዉት” አልኳቸው፤ እነርሱም የአገልግሎቴን ዋጋ ሠላሳ ብር ሰጡኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “የሚበጅ መስሎ ከታያችሁ ዋጋዬን ክፈሉኝ፤ አይሆንም ካላችሁም ተዉት” አልኋቸው፤ ስለዚህ ሠላሳ ብር ከፈሉኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ “ደስ ብሎአችሁ እንደሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፥ ያለዚያ ግን ተውት” አልኩት። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፦ ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፣ ያለዚያ ግን ተውት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፥ ያለዚያ ግን ተውት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ። |
የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።
አንድ ቀን አክዓብ ናቡቴን “የወይን ተክል ቦታህን ስጠኝ፤ በቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ የአትክልት ቦታ ላደርገው እፈልጋለሁ፤ በምትኩ ከእርሱ የተሻለ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ልትሸጠው ብትፈልግም የተሻለ ጥሩ ዋጋ እከፍልሃለሁ” አለው።
ስለዚህ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቈርጡ ሰዎችን ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፤ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደርጋለሁ፤ ለሰዎችህም አንተ የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተ እንደምታውቀው የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቈራረጥ የአንተን ሰዎች ያኽል ዕውቀት የላቸውም።”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ራት ይበሉ ነበር፤ የስምዖን ልጅ አስቆሮታዊው ይሁዳ ግን ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ ዲያብሎስ በልቡ ክፉ ሐሳብ አሳደረበት።