Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 37:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማኤላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጒድጓድ ጐትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይዘውት ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የምድያም ነጋዶችም አለፉ፥ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጉድጓድ አወጡት፥ ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሃያ ብር ሸጡት፥ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የምድያም ነጋዶችም አለፈ እነርሱም ዮሴፍን አንሥተው ከጕድጓድ አወጡት ለእስማኤላውያንም ዮሴፍን በሀያ ብር ሸጡት እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወሰዱት።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 37:28
25 Referencias Cruzadas  

እርስዋም ዚምራንን፥ ዮቅሻንን፥ መዳንን፥ ምድያምን፥ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት።


ከዚህ በኋላ ምሳ ለመብላት ተቀመጡ፤ በሚመገቡበትም ጊዜ እስማኤላውያን ነጋዴዎችን በሩቅ አዩ፤ እነርሱም በግመሎቻቸው ቅመማ ቅመም፥ በለሳን፥ ከርቤም ጭነው ከገለዓድ ወደ ግብጽ የሚጓዙ ነበሩ።


በዚያን ጊዜ የምድያም ሰዎች እስማኤላውያን ዮሴፍን በግብጽ አገር ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር ከፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ የሆነ የዘበኞቹ አለቃ ነበር።


እስማኤላውያን ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት፤ እዚያም ከግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ባለሥልጣኖች አንዱ ለሆነው ለጶጢፋር ሸጡት፤ ጶጢፋር የተባለው ግብጻዊ፥ የፈርዖን የዘበኞች አለቃ ነበር።


እኔ ከዕብራውያን አገር ወደዚህ የመጣሁት ወድጄ ሳይሆን ተሸጬ ነው፤ እዚህም አገር ከመጣሁ ወዲህ በእስር ቤት የምገኘው ምንም በደል ሳልፈጽም ነው።”


የዮሴፍ ወንድሞች አባታቸው ከሞተ በኋላ “ዮሴፍ ባደረስንበት በደል ሁሉ እስከ አሁንም ቂም ይዞ ሊበቀለን ቢፈልግ ምን እናደርጋለን?” ተባባሉ።


ነገር ግን ከእነርሱ አንዱን ሰው አስቀድሞ ላከ፤ እርሱም እንደ ባሪያ የተሸጠው ዮሴፍ ነበር።


በምድያማውያን፥ በሲሣራና በያቢንም ላይ በቂሾን ወንዝ ያደረግኸውን በእነዚህም ላይ አድርግ።


አንድ የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ውሃ ለመቅዳትና በገንዳ እየሞሉ የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማጠጣት ወደዚያ መጡ።


“ሊሸጠው ወይም ባርያ አድርጎ ሊገዛው አስቦ ሰውን አፍኖ የሚወስድ ሁሉ በሞት ይቀጣ።


ከምድያምና ከኤፋ የመጡት ግመሎች ምድራችሁን ሞሉት። ወርቅና ዕጣን ይዘው ከሳባ የመጡት ሁሉ እግዚአብሔርን በከፍተኛ ድምፅ ያመሰግኑታል።


እነርሱም ከዚያ ጒድጓድ ውስጥ በዚያው ገመድ ስበው አወጡኝና በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ ዘጉብኝ።


ከአምስት እስከ ኻያ ዓመት ለሆነው ወንድ ኻያ ጥሬ ብር ይሁን፤ በዚሁ ዕድሜ ክልል ላለች ሴት ዐሥር ጥሬ ብር ይሁን፤


የሴቲቱም ስም ኮዝቢ ይባል ነበር፤ “ጹር” ተብሎ የሚጠራው አባትዋም በአንድነት የሚኖሩ የጥቂት ምድያማውያን ጐሣዎች አለቃ ነበር።


“በምድያማውያን ላይ አደጋ ጥላችሁ ደምስሱአቸው፤


“ኢየሱስን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?” አለ። እነርሱም ሠላሳ ጥሬ ብር ሰጡት


በዚህ ሁኔታ “የእስራኤል ልጆች የገመቱትን ለእርሱ ዋጋ የሚሆን ሠላሳ ጥሬ ብር ወሰዱ፤


“የያዕቆብ ልጆች በወንድማቸው በዮሴፍ ላይ ቀንተው በግብጽ አገር ባሪያ እንዲሆን ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤


ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ጌዴዎንን “አንተ ከምድያማውያን እጅ አድነኸናልና አንተና ከአንተም በኋላ ልጆችህ እንዲሁም የልጅ ልጆችህ ገዢዎቻችን ሁኑ፤” አሉት።


እስማኤላውያን የጆሮ ጉትቻ ማድረግ ልማዳቸው ስለ ነበረ የጌዴዎን ወታደሮች ጉትቻዎቻቸውን ማርከው ነበር፤ ጌዴዎንም “እያንዳንዳችሁ የማረካችሁትን ጉትቻ ስጡኝ” ብሎ ለመናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos