ሮሜ 8:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ስለማናውቅ መንፈስ ቅዱስ በድካማችን ይረዳናል፤ በቃል ሊገለጥ በማይቻል መቃተት ያማልደናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ይማልድልናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ደግሞ መንፈስ በድካማችን ይረዳናል፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ለእኛ ያማልድልናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንፈስ ቅዱስም ከድካማችን ይረዳናል፤ እንግዲያስ ተስፋችንን ካላወቅን ጸሎታችን ምንድነው? ነገር ግን እርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ስለ መከራችንና ስለ ችግራችን ይፈርድልናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ |
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
ኢየሱስ ግን “እናንተ የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ በቅርብ ጊዜ የምጠጣውን የመከራ ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?” አላቸው። እነርሱም “አዎ እንችላለን!” አሉ።
ስለዚህ “አባ! አባታችን ሆይ!” ብላችሁ የምትጠሩበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ በፍርሃት ለመኖር እንደገና የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም።
በዚህ እንደ ምድራዊ ድንኳን በሆነው ሥጋችን ውስጥ ስንኖር ከብደን እንቃትታለን፤ የምንቃትተውም ሞት በሕይወት እንዲለወጥ ሰማያዊውን አካል በበለጠ እንድንለብስ ነው እንጂ ከዚህ ከምድራዊ ሥጋችን ለመለየት በመፈለግ አይደለም።