Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 102:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ድምፄን ከፍ አድርጌ በመቃተቴ ከቈዳና ከአጥንት በቀር ሰውነት የለኝም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣ ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋራ ተጣበቀ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ልቤም እንደ ተመታ ሣር ደረቀ፤ እህል መብላትም ተረሳኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ምኞ​ት​ህን ከበ​ረ​ከቱ የሚ​ያ​ጠ​ግ​ባት፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ት​ህን እንደ ንስር የሚ​ያ​ድ​ሳት፥

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 102:5
10 Referencias Cruzadas  

ሥጋዬ አልቆ ቆዳዬ በአጥንቴ ላይ ተጣበቀ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ ተረፍኩ።


አሁን ግን ፊታቸው እንደ ጥላሸት ስለ ጠቈረ፥ በየመንገዱ ወድቀው ሲገኙ የሚያውቃቸው የለም፤ እንደ እንጨት የደረቀ ቆዳቸው በአጥንታቸው ላይ ተጣብቆአል።


ደስተኛነት ለልብ መልካም መድኃኒት ነው፤ የመንፈስ ሐዘንተኛ መሆን ግን አጥንትን ይሰብራል።


እግዚአብሔር የለቅሶዬን ጩኸት ሰምቶአል፤ ስለዚህ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ!


ከሐዘኔ ብዛት የተነሣ ደክሜአለሁ፤ ከለቅሶዬ ብዛት የተነሣ በየሌሊቱ አልጋዬ በእንባ ይረጥባል፤ ትራሴም ይርሳል።


ይህም ሳይቋረጥ በየዓመቱ የሚደጋገም ነገር ነበር፤ ይኸውም ወደ እግዚአብሔር ቤት በሄዱ ቊጥር ሐና እያለቀሰች ምግብ ለመብላት እምቢ እስከምትል ድረስ ጵኒና በብርቱ ታበሳጫት ነበር።


እንደ አበባ ታይቶ ወዲያውኑ ይረግፋል፤ እንደ ጥላም ብዙ ሳይቈይ ወዲያው ያልፋል።


ሣር ወዲያው አድጎ ያብባል፤ ሲመሽ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios