ከዚህ በኋላ ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ ሲል ጠየቀው “ይህ ያደረግኽብኝ ነገር ምንድን ነው? ሣራይ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልነገርከኝም?
ሮሜ 4:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም የጸደቀው በሥራ ቢሆን ኖሮ፥ የሚመካበት ነገር ባገኘ ነበር፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ፊት መመካት አይችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን ኖሮ፣ የሚመካበት ነበረው፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት መመካት አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፤ በእግዚአብሔር ፊት ግን መመካት አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃም በሥራው ጸድቆስ ቢሆን ትምክሕት በሆነው ነበር፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። |
ከዚህ በኋላ ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ ሲል ጠየቀው “ይህ ያደረግኽብኝ ነገር ምንድን ነው? ሣራይ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልነገርከኝም?
አንተ ከሌሎች በምን ትበልጣለህ? ከሌላ ያልተቀበልከውስ ነገር ምን አለ? ታዲያ፥ ሁሉን ነገር የተቀበልከው ከሌላ ከሆነ እንዳልተቀበለ ሰው ስለምን ትመካለህ?
እነዚያ ሌሎች ሐዋርያት “እኛም እንደ እነርሱ እንሠራለን” እያሉ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የማደርገውን ወደፊትም ደግሞ አደርጋለሁ።
በልብ ባለው ሳይሆን በሚታየው ለሚመኩ መልስ ለመስጠት እንድትችሉ በእኛ ትመኩ ዘንድ ዕድል እንሰጣችኋለን እንጂ እንደገና እኛ ለእናንተ ራሳችንን አናመሰግንም።
ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የተስፋ ቃል ለሚያምኑ እንዲሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው ዓለም በሙሉ ለኃጢአት በመገዛት የኃጢአት እስረኛ ሆኖአል።
ይህንንም የማደርግበት ምክንያት በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴን ጽድቅ ትቼ በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ለማግኘትና ከእርሱም ጋር ለመሆን ነው።
ኢያሱም ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ ‘ከብዙ ዘመናት በፊት የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ባዕዳን አማልክትን በማምለክ ይኖሩ ነበር፤ ከነዚያም አባቶች አንዱ የአብርሃምና የናኮር አባት ታራ ነበር፤