ሮሜ 1:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እግዚአብሔርን ዐውቀውት ሳለ ለእርሱ እንደ አምላክነቱ የሚገባውን ክብርና ምስጋና አልሰጡትም፤ በሐሳባቸውም ከንቱ ሆኑ፤ የማያስተውል ልቡናቸውም ጨለመ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም እግዚአብሔርን እያወቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን አላከበሩትም ወይም አላመሰገኑትም፤ ነገር ግን ምክንያታቸው ዋጋ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን ሲያውቁት እንደ እግዚአብሔርነቱ አላከበሩትም፤ አላመሰገኑትምም፤ ነገር ግን ካዱት፤ በአሳባቸውም ረከሱ፤ ልቡናቸውም ባለማወቅ ጨለመ። |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።
ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖች ንጉሥ ቤንሀዳድን እንዲህ አሉት፤ “የእስራኤል አማልክት የተራራ አማልክት ናቸው፤ እስራኤላውያን እኛን ማሸነፍ የቻሉት ስለዚህ ነው፤ በሜዳማ ስፍራዎች ጦርነት ብንገጥማቸው ግን እናሸንፋለን፤
የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! የምትጠብቀኝና ብርታትን የምትሰጠኝ አንተ ነህ፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ አምባዬ ነህ፤ ሕዝቦች ከምድር ዳርቻ ሁሉ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፦ “የቀድሞ አባቶቻችን ከሐሰተኞች አማልክት በቀር ምንም አልነበራቸውም፤ ጣዖቶቻቸው ሁሉ የማይጠቅሙ ከንቱዎች ነበሩ፤
እነሆ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኔ ርቀው የሄዱት በኔ ላይ ምን ጥፋት አግኝተው ነው? እነርሱም ከንቱ የሆኑትን ጣዖቶች በማምለካቸው ራሳቸውን ከንቱዎች አደረጉ።
እርስዋ እህልን፥ የወይን ጠጅን፥ የወይራ ዘይትን የሰጠኋት፥ እኔ እንደ ሆንኩ ከቶ አልተገነዘበችም፤ እኔ ያበዛሁላትን ብርና ወርቅ “በዓል” ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት አቀረበች።
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ የሆነበትም ሌላው ምክንያት አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ እንዲያመሰግኑት ነው፤ ይህም፦ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም በዝማሬ ምስጋና አቀርባለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
በእኩለ ቀን እንደ ዕውር ትደናበራለህ፤ የምትሄድበትንም መንገድ ማግኘት አትችልም፤ የምትሠራውም ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ዘወትር ጭቈናና ምዝበራ ይደርስብሃል፤ የሚረዳህም ሰው አታገኝም።
ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፥ ለገንዘብ የሚስገበገቡ፥ ትምክሕተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ ውለታቢሶች፥ ቅድስና የሌላቸው፥
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
በታላቅ ድምፅም “እግዚአብሔርን ፍሩ! አክብሩትም! የእርሱ የፍርድ ሰዓት ደርሶአል፤ ሰማይንና ምድርን ባሕርንና የውሃ ምንጮችን ለፈጠረ አምላክ ስገዱ!” አለ።
ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”