ራእይ 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትዕግሥት መጽናትህንና ስለ ስሜም ሳትሰለች መከራ መቀበልህን ዐውቃለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በትዕግሥት መጽናትህንና ስለ ስሜም መከራ መቀበልህን ዐውቃለሁ፤ በዚህ ሁሉ አልታከትህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትዕግስት መጽናትህንና ስለ ስሜ መከራ መቀበልህን አውቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታግሠህማል፤ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታግሠህማል፥ ስለ ስሜም ብለህ ጸንተህ አልደከምህም። |
እግዚአብሔርን በድዬዋለሁ፤ ስለዚህም እርሱ የቀረበብኝን ክስ ተመልክቶ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቊጣውን እታገሣለሁ፤ በመጨረሻም እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል፤ ፍትሕንም ይሰጠኛል።
ሲሄዱም ሳሉ የቀሬና ሰው የሆነውን የእስክንድርንና የሩፎስን አባት ስምዖንን ከገጠር ወደ ከተማ ሲገባ አገኙት፤ የኢየሱስን መስቀል እንዲሸከም አስገደዱት።
በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር የሚያመለክተው ግን በመልካምና በቅን ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁትን ነው፤ እነርሱ በቃሉ ጸንተው ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።”
በጌታ አገልግሎት ለሚደክሙት ለትሩፋይናና ለትሩፎሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ አገልግሎት እጅግ ለደከመችውና በክርስቶስ ለምወዳት ለፔርሲስ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ከወሰነልን ክልል አልፈን በሌሎች ሥራ ያለ ልክ አንመካም፤ ይልቅስ እምነታችሁ እንዲያድግና የእኛም ሥራ እግዚአብሔር በወሰነልን ክልል በእናንተ መካከል ይበልጥ እንዲስፋፋ ተስፋ እናደርጋለን።
እነርሱ የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እኔ ከእነርሱ ይበልጥ የክርስቶስ አገልጋይ ነኝ፤ ይህንንም ስል እንደ እብድ ሆኜ ነው የምናገረው፤ ከእነርሱ ይበልጥ ብዙ ጊዜ በሥራ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ታስሬአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ተገርፌአለሁ፤ ብዙ ጊዜ ለሞት አደጋ ደርሼአለሁ፤
ይህም የሚሆነው ሕይወት የሚገኝበትን ቃል ሳታቋርጡ አጥብቃችሁ በመያዝ ነው፤ በዚህ ዐይነት ሩጫዬም ሆነ ሥራዬ ከንቱ ሆኖ ስለማይቀር ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ የምመካበት ምክንያት ይኖረኛል ማለት ነው።
አንተም እዚያ ያለኸው ታማኝ የሥራ ጓደኛዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ፤ እነዚህ ሴቶች ከእኔ ጋር ከቀሌምንጦስና ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎችም የሥራ ጓደኞቼ ጋር በመሆን ወንጌልን በማዳረስ ረገድ ተጋድለዋል።
በአምላካችንና በአባታችን ፊት እምነታችሁ የሚሠራውን፥ ለፍቅር የምታደርጉትንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ተስፋ በትዕግሥት መጠባበቃችሁን ሳናቋርጥ እናስታውሳለን።
ወንድሞች ሆይ! እንዴት እንደ ሠራንና እንደ ደከምን ታውቃላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ በምናበሥርበት ጊዜ በአንዳችሁም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን በመሥራት እንደክም ነበር።
ወንድሞች ሆይ! በእናንተ መካከል በሥራ የሚደክሙትን፥ በጌታ ኢየሱስ አለቆቻችሁንና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን እንድታከብሩአቸው እንለምናችኋለን፤
የማንንም እንጀራ በብላሽ አልበላንም፤ ይልቅስ ከእናንተ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆንበት በማለት ሌሊትና ቀን በመድከምና በመልፋት እንሠራ ነበር።
እንደ ደመና በዙሪያችን የከበቡን እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ስላሉን እኛ እንደ ሸክም የሆነብንን ነገር ሁሉ በእኛ ላይ የተጣበቀብንን ኃጢአት አስወግደን በፊታችንም ያለውን የሩጫ እሽቅድድም በትዕግሥት በመጽናት እንሩጥ።
በኢየሱስ ክርስቶስ የመከራውና የመንግሥቱ እንዲሁ የትዕግሥቱ ከእናንተ ጋር ተካፋይ የሆንኩ እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ታስሬ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርኩ፤
ትዕግሥተኛ ሁን ያልኩህን ቃሌን ስለ ጠበቅህ እኔም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሊፈትናቸው በዓለም ሁሉ ላይ ከሚመጣው ከመከራ ሰዓት እጠብቅሃለሁ።