የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
ራእይ 13:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለመማረክ የተመደበ ይማረካል፤ በሰይፍ ለመገደል የተመደበ በሰይፍ ይገደላል፤” እንግዲህ የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት የሚያስፈልገው በዚህ ጊዜ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም የሚማረክ ቢኖር፣ እርሱ ይማረካል፤ ማንም በሰይፍ የሚገደል ቢኖር፣ እርሱ በሰይፍ ይገደላል። ይህም የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት የሚታየው በዚህ እንደ ሆነ ያስገነዝባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመማረክ የተመደበ ወደ ምርኮ ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ መገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይማረክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ወደ ምርኮነት ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል። የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው። |
የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።
አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።
‘ታዲያ ወዴት እንሂድ?’ ብለው ቢጠይቁህ፥ ከዚህ በፊት እንዲህ ብዬ የነገርኳቸውን አስታውሳቸው፤ ‘በመቅሠፍት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በመቅሠፍት ይሞታሉ! በጦርነት እንዲሞቱ የተፈረደባቸው በጦርነት ይሞታሉ! በራብ እንዲሞቱ የተፈረደባቸውም በራብ ይሞታሉ። ተማርከው እንዲታሰሩ የተፈረደባቸው ወደ ምርኮ ይሂዱ።’
ናቡከደነፆር መጥቶ ግብጽን ድል ይነሣል፤ በበሽታ እንዲሞቱ የተወሰነባቸው በበሽታ ይሞታሉ፤ ተማርከው እንዲወሰዱ የተወሰኑ ይማረካሉ፤ በጦርነት እንዲሞቱ የተወሰኑ በጦርነት ይገደላሉ።
ምክንያቱም ራእዩ የተወሰነለትን ጊዜ ይጠብቃል፤ እርሱም የሚናገረው የሚፈጸምበትን ቀን ነው፤ ሐሰትም የለበትም፤ ጊዜ የሚወስድ ቢመስልም ጠብቅ፤ በእርግጥ ይደርሳል፤ አይዘገይምም።
በኢየሱስ ክርስቶስ የመከራውና የመንግሥቱ እንዲሁ የትዕግሥቱ ከእናንተ ጋር ተካፋይ የሆንኩ እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ታስሬ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርኩ፤
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”
ያየኸው አውሬ ቀድሞ ነበር፤ አሁን የለም፤ በኋላ ከጥልቁ ጒድጓድ ይወጣል፤ ወደ ጥፋቱም ይሄዳል፤ ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ የምድር ኗሪዎች፥ አውሬው ቀድሞ የነበረ፥ አሁን የሌለ፥ በኋላ የሚመጣ መሆኑን ሲያዩ ይደነቃሉ።
ሥራህን፥ ጥረትህንና ትዕግሥትህን ዐውቃለሁ፤ ክፉዎችን ግን ልትታገሣቸው እንዳልቻልክ፥ ሐዋርያት ሳይሆኑም ሐዋርያት ነን የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው ዐውቃለሁ።
ትዕግሥተኛ ሁን ያልኩህን ቃሌን ስለ ጠበቅህ እኔም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሊፈትናቸው በዓለም ሁሉ ላይ ከሚመጣው ከመከራ ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
እንግዲህ ምን ዐይነት ትምህርት እንደ ተቀበልክና እንደ ሰማህ አስታውስ፤ ጠብቀውም፤ ንስሓም ግባ፤ ባትነቃ ግን እንደ ሌባ በድንገት እመጣብሃለሁ፤ በምን ሰዓት ወደ አንተ እንደምመጣ አታውቅም።