| ራእይ 17:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ያየኸው አውሬ ቀድሞ ነበር፤ አሁን የለም፤ በኋላ ከጥልቁ ጒድጓድ ይወጣል፤ ወደ ጥፋቱም ይሄዳል፤ ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ የምድር ኗሪዎች፥ አውሬው ቀድሞ የነበረ፥ አሁን የሌለ፥ በኋላ የሚመጣ መሆኑን ሲያዩ ይደነቃሉ።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ያየኸው አውሬ ቀደም ሲል ነበረ፤ አሁን ግን የለም፤ በኋላም ከጥልቁ ጕድጓድ ይወጣል፤ ወደ ጥፋቱም ይሄዳል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ የምድር ነዋሪዎች አውሬው ቀድሞ የነበረ፣ አሁን ግን የሌለ፣ በኋላም የሚመጣ መሆኑን ሲያዩ ይደነቃሉ።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁን ግን የለም፤ ከጥልቁም ሊወጣ ነው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ የምድር ኗሪዎች አውሬው አስቀድሞ እንደ ነበረ አሁን ደግሞ እንደሌለ፥ ነገር ግን ተመልሶ እንደሚመጣ ሲያዩ ይደነቃሉ።Ver Capítulo የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁንም የለም፤ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ።Ver Capítulo |