ኤርምያስ 43:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ናቡከደነፆር መጥቶ ግብጽን ድል ይነሣል፤ በበሽታ እንዲሞቱ የተወሰነባቸው በበሽታ ይሞታሉ፤ ተማርከው እንዲወሰዱ የተወሰኑ ይማረካሉ፤ በጦርነት እንዲሞቱ የተወሰኑ በጦርነት ይገደላሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እርሱም መጥቶ ግብጽን ይወጋል፤ ሞት የሚገባቸውን ለሞት፣ ለምርኮ የተመደቡትን ወደ ምርኮ፣ ለሰይፍ የተዳረጉትን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 መጥቶም የግብጽን ምድር ይመታል፥ ለሞትም የሚሆነውን ለሞት፥ ለምርኮም የሚሆነውን ለምርኮ፥ ለሰይፍም የሚሆነውን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 መጥቶም የግብፅን ምድር ይመታል፤ ለሞትም የሚሆነውን ለሞት፥ ለምርኮም የሚሆነውን ለምርኮ፥ ለሰይፍም የሚሆነውን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 መጥቶም የግብጽን ምድር ይመታል፥ ለሞትም የሚሆነውን ለሞት፥ ለምርኮም የሚሆነውን ለምርኮ፥ ለሰይፍም የሚሆነውን ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል። Ver Capítulo |
ከጽዋው መጠጣት የሚገባቸው ሌሎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የግብጽ ንጉሥ ከባለሟሎቹና ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር፥ የግብጽ ሕዝብና በግብጽ የሚኖሩ መጻተኞች ሁሉ፥ በዑፅ ምድር የሚኖሩ ነገሥታት ሁሉ፥ በፍልስጥኤማውያን ከተሞች፥ በአስቀሎና፥ በጋዛ፥ በዔቅሮንና በአሽዶድ፥ በሌሎች ቦታዎችም የሚኖሩ የኤዶም፥ የሞአብና የዐሞን ሕዝቦች ሁሉ፥ የጢሮስና የሲዶና ነገሥታት ሁሉ፥ በሜዲትራኒያን ባሕር ዙሪያ በሚገኙ አገሮች ያሉ ነገሥታት ሁሉ፥ የደዳን፥ የቴማና የቡዝ ከተሞች ሁሉ፥ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የሚላጩ ሕዝቦች ሁሉ፥ የዐረብ አገር ነገሥታት ሁሉ፥ በበረሓ የሚኖሩ ነገዶች ነገሥታት ሁሉ፥ የዘምሪ፥ የዔላምና የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፥ ሌሎችም በስተሰሜን በኩል በሩቅና በቅርብ ያሉ ነገሥታት ሁሉ በየተራቸው። በምድር ላይ የሚኖሩት ሕዝብ ሁሉ፥ ከዚህ ጽዋ ይጠጣሉ፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ከዚህ ጽዋ መጠጣት ይኖርበታል።