ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ።
መዝሙር 99:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋኑ ተቀመጠ፤ ምድርም ትናወጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ነገሠ፤ ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤ በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጧል፤ ምድር ትናወጥ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፥ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥ |
ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ ዙፋኑን የዘረጋውን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የቃል ኪዳኑን ታቦት ለማምጣት ወደ በዓለ ይሁዳ ሄዱ።
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ በመክደኛው ላይ በተሠሩት ክንፍ ባላቸው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ ለእስራኤል ሕዝብ የምታቀርበውን ትእዛዞቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ።
የተዘበራረቀ ምክር እንዲሰጡ ያደረጋቸውም እግዚአብሔር ነው፤ በመጨረሻም ግብጽ በሁሉ ነገር በመሳሳት የገዛ ትፋቱ አዳልጦት እንደሚጥለው ሰካራም ትንገዳገዳለች።
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ታዲያ ስለምን አታከብሩኝም? በፊቴስ ለምን አትንቀጠቀጡም፤ አሸዋን ውሃ አልፎት እንዳይሄድ ለዘለዓለሙ የባሕር ወሰን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤ ባሕር የቱንም ያኽል ቢናወጥ፥ ማዕበል፥ ሞገዱም ቢያስገመግም፥ ወሰን የሆነውን የአሸዋ ግድብ አልፎ መሄድ አይችልም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህ በእስራኤላውያን መካከል ለዘለዓለም በምኖርበት ዙፋኔና የእግሬ ማሳረፊያ ነው፤ እስራኤላውያንና ንጉሦቻቸው ከእንግዲህ ወዲህ ጣዖት በማምለክና በንጉሦቻቸው ሞት ጊዜ በሚያደርጉአቸው ድርጊቶች ስሜን አያሰድቡም።
ወዳጆቼ ሆይ! እኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ሁልጊዜ ታዛዦች እንደ ነበራችሁ፥ ይልቁንም አሁን ከእናንተ በራቅሁበት ጊዜ ይበልጥ ታዛዦች እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ፤ ስለዚህ እያንዳንዳችሁ መዳናችሁን ፍጹም ለማድረግ በፍርሃትና በአክብሮት ተግታችሁ ሥሩ።
እንዲህም አሉ፦ “ያለህና የነበርክ፤ ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ትልቁን ሥልጣንህን በእጅህ ስላደረግህና ስለ ነገሥክ እናመሰግንሃለን።