መዝሙር 93:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤ ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው። |
ብልጽግናና ክብር ሁሉ የሚገኘው ከአንተ ነው፤ አንተ ሁሉን ትገዛለህ፤ ኀይልና ብርታት ያንተ ናቸው፤ የወደድከውንም ታላቅና ብርቱ ማድረግ ይቻልሃል።
ግዛትህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። መንግሥትህም ዘለዓለማዊ ነው። እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ የታመነ ነው፤ እርሱ የሚያደርገው ሁሉ መልካም ነው።
በቊጣህ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም ደምስሳቸው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያስተዳድርና ግዛቱም በምድር ሁሉ እንደ ተንሰራፋ፥ ሰው ሁሉ ያውቃል።
ምድርን የፈጠርኩና ሰውንም ፈጥሬ በእርስዋ እንዲኖር ያደረግኹ እኔ ነኝ፤ ሰማያትን በኀይሌ የዘረጋሁና ሠራዊቶቻቸውን የምቈጣጠር እኔ ነኝ።”
ሰማያትን የፈጠረው እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድር ቅርጽ ሰጥቶ የሠራት፥ የመሠረታትም እርሱ ነው፤ የፈጠራትም መኖሪያ እንድትሆን ነው እንጂ፥ ቅርጽ የሌላትና ባዶ እንድትሆን አይደለም፤ እርሱ፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ።
ቃሌን በአንደበትሽ አሳድራለሁ፤ አንቺንም በእጄ ጥላ ሥር እጋርድሻለሁ፤ ሰማያትን የዘረጋሁ፥ ምድርንም የመሠረትኩ እኔ ነኝ፤ ጽዮንንም ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ እላታለሁ።”
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
በተራሮች ላይ ስለ ሰላምና ስለ መዳን የሚናገር፥ መልካም ዜናንም የሚያበሥር፥ “አምላክሽ ይነግሣል!” ብሎ ለጽዮን የሚነግራት የመልክተኛ እግሩ ምንኛ ድንቅ ነው!
ከኤዶም ቦጽራ ቀይ መጐናጸፊያ ተጐናጽፎ የሚመጣው ይህ ማነው? በታላቅ ኀይሉ አስደናቂ ልብስ ለብሶ የሚራመደው ይህ ማነው? “ፍርድን የምሰጥ የማዳን ኀይል ያለኝ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
የብዙ ሰዎችን ድምፅ የወራጅ ውሃን ድምፅ፥ የብርቱ ነጐድጓድንም ድምፅ፥ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚችል ጌታ አምላካችን ይነግሣል!