Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 93:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘመናት ሁሉ በፊት አምላክ ነህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፥ አንተም ከዘለዓለም ጅምሮ አለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የም​ድር ፈራጅ፥ ከፍ ከፍ አለ፤ ለት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ፍዳ​ቸ​ውን ክፈ​ላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 93:2
15 Referencias Cruzadas  

አምላክ ሆይ! ዙፋንህ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የጸና ነው። በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው።


ተራራዎችን ከመሥራትህና ዓለምንም ከመፍጠርህ በፊት፥ አንተ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላክ ነህ።


ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትም ዛሬም ለዘለዓለምም ያው ነው፤ አይለወጥም።


“ለሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ የመጀመሪያና የመጨረሻ ከሆነው፥ ሞቶ ከነበረውና ሕያው ከሆነው የተነገረ ነው፤


“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”


ያለው፥ የነበረው፥ የሚመጣውም ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር “አልፋና ዖሜጋ፥ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ!” ይላል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በኤፍራታ ምድር የምትገኚ ቤተልሔም ሆይ! ከይሁዳ ትናንሽ ከተሞች አንድ ብትሆኚም እንኳ ከአንቺ አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ የእስራኤልን ሕዝብ የሚመራ ገዢ ይወጣልኛል።”


ንጉሡ ናቡከደነፆር እንዲህ አለ፦ “ሰባቱ ዓመቶች ካለፉ በኋላ ቀና ብዬ ወደ ሰማይ ተመለከትኩ፤ አእምሮዬም ተመለሰልኝ፤ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤ ለዘለዓለማዊው አምላክ ክብርና ውዳሴ አቀረብኩ፤ “ግዛቱ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፤


ግዛትህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል። መንግሥትህም ዘለዓለማዊ ነው። እግዚአብሔር በቃል ኪዳኑ የታመነ ነው፤ እርሱ የሚያደርገው ሁሉ መልካም ነው።


ጓደኛዬ ወዳጆቹን አጠቃቸው፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ።


“እኔም እየተመለከትኩ ሳለሁ ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ያ ጥንታዊው በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ፥ ጠጒሩም እንደ ነጭ ሱፍ ነበር፤ ዙፋኑና የዙፋኑ መንኰራኲር እንደሚነድ እሳት ይንበለበሉ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios