መዝሙር 92:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉዎች እንደ ሣር ቶሎ ቢያድጉም፥ ክፉ አድራጊዎች ቢበለጽጉም፥ እነርሱ ለዘለዓለሙ ይጠፋሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ ለዘላለሙ ይጠፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማያስተውል ሰው አያውቅም። አላዋቂ አይረዳውም። |
የሕዝቦቻቸው ኀይል ተዳክሞአል፤ እነርሱም ተስፋ ቈርጠው ዐፍረዋል፤ እንደ ሜዳ አበባ፥ እንደ ለጋ ሣር፥ በጣራ ላይ እንደሚበቅልና ፈጥኖ እንደሚጠወልግ ጓሳ ናቸው።
እንደምናየው ከሆነ እነሆ፥ ክፉ አድራጊዎች ዕድለኞች ናቸው፤ በእርግጥም እነርሱ በብልጽግና ይኖራሉ፤ እግዚአብሔርን እንኳ እየተፈታተኑት ምንም ችግር አይደርስባቸውም እያላችሁ ትናገራላችሁ።’ ”
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።