መዝሙር 92:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ነገር የማይገባው አላዋቂ ለሆነ ሰው ነው፤ ሞኝ ሰውም ቢሆን አይገባውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤ ሞኝም አያስተውለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ሥራህ እንዴት ትልቅ ነው! ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው! |
ሞኞች በልባቸው፦ “እግዚአብሔር የለም” ይላሉ፤ እንደነዚህ ያሉት የተበላሹ ናቸው፤ አጸያፊ ድርጊቶችንም ይፈጽማሉ፤ ከእነርሱ መካከል መልካም ነገርን የሚያደርግ አንድም የለም።
እንዲገቱ ለማድረግ በልባብና በልጓም እንደሚመሩት እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ የማይገባችሁ አትሁኑ። እንደዚያ ካላደረጋችሁ ፈረስና በቅሎ ወደ እናንተ አይቀርቡም።
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
ዓላማህ ታላቅ ነው፤ ሥራህም ኀያል ነው፤ ሕዝቦች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ታያለህ፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደአካሄዱና እንደየሥራው ዋጋውን ትከፍላለህ።
የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሥጋዊ ሰው ግን ከእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠውን ስጦታ መቀበል አይችልም፤ የስጦታው ታላቅነት የሚመረመረው በእግዚአብሔር መንፈስ አማካይነት ስለ ሆነ ሊያስተውለው አይችልም፤ እንዲያውም ይህ ለእርሱ ሞኝነት መስሎ ይታየዋል።