ከእነዚህ ካዘጋጀኋቸው ነገሮች ሁሉ በላይ እኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካለኝ ታላቅ ፍቅር የተነሣ ከራሴ ንብረት ብዙ ብርና ወርቅ ሰጥቼአለሁ፤
መዝሙር 91:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለሚወደኝ ከጠላቶቹ እጅ አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም ስለሚያውቅ እጠብቀዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወድዶኛልና እታደገዋለሁ፤ ስሜን ዐውቋልና እከልለዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፥ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜ በመልካም ሽምግልና ይበዛሉ፤ ዕረፍት ያላቸውም ሆነው ይኖራሉ። |
ከእነዚህ ካዘጋጀኋቸው ነገሮች ሁሉ በላይ እኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ካለኝ ታላቅ ፍቅር የተነሣ ከራሴ ንብረት ብዙ ብርና ወርቅ ሰጥቼአለሁ፤
ከአሀዋ ወንዝ ተነሥተን ወደ ኢየሩሳሌም ጒዞ የጀመርነውም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ነበር፤ በምንጓዝበትም ጊዜ አምላካችን ከእኛ ጋር ስለ ነበር ከጠላት አደጋና ከደፈጣ ተዋጊዎች ሽመቃ ጠበቀን።
አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችኋል፤ ይልቁንም እግዚአብሔር እናንተን ዐውቋችኋል፤ ታዲያ፥ ወደ እነዚያ ወደ ደካሞችና ወደማይረቡት የዓለም ሥርዓቶች እንዴት ተመለሳችሁ? እንዴትስ እንደገና የእነርሱ ባሪያዎች ለመሆን ትፈልጋላችሁ?
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?