Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 91:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አንበሳንና እባብን ትረግጣለህ፤ በአስፈሪው አንበሳና በመርዛሙ እባብ ላይ ትራመዳለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በአንበሳና በእፉኝት ላይ ትጫማለህ፤ ደቦሉን አንበሳና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፥ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የተ​ተ​ከሉ ናቸው፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አደ​ባ​ባይ ውስጥ ይበ​ቅ​ላሉ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 91:13
14 Referencias Cruzadas  

እነሆ! እባብንና ጊንጥን እንድትረግጡ፥ የጠላትንም ኀይል ሁሉ እንድትቋቋሙ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፤ የሚጐዳችሁ ምንም ነገር የለም።


አንበሶቹ እንዳይጐዱኝ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ አፋቸውን ዘጋ፤ ይህንንም ያደረገው እኔ በእርሱ ዘንድ ንጹሕ መሆኔንና አንተንም አለመበደሌን ስላወቀ ነው።”


እባቦችን ቢይዙ፥ ወይም የሚገድል መርዝ እንኳ ቢጠጡ አይጐዳቸውም፤ እጃቸውን በበሽተኞች ላይ ሲጭኑ በሽተኞቹ ይድናሉ።”


ከአንበሳና ድብ ያዳነኝ እግዚአብሔር ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሳኦልም “መልካም ነው! እንግዲህ ሂድ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን!” ሲል መለሰለት።


ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ።


ይህን ብታደርጉ የሰላም አምላክ ፈጥኖ ሰይጣንን በእግራችሁ ሥር ይቀጠቅጥላችኋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል።


ታላቁም ዘንዶ ወደታች ተጣለ፤ እርሱ መላውን ዓለም የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞው እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።


እነርሱ እንደ እባብ መርዘኞች ናቸው፤ እንደ ደንቆሮ እፉኝትም ጆሮአቸውን ይደፍናሉ።


ሰውን የሚጐዳ ክፉ ቃል ለመናገር አፋቸው እንደ መቃብር የተከፈተ ነው፤ በምላሳቸው ያታልላሉ፤ የከንፈራቸውም ንግግር እንደ እባብ መርዝ የሚጐዳ ነው፤


በምታርሰው መሬት ላይ ድንጋይ አያውክህም፤ ከአራዊትም ጋር በሰላም ትኖራለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios