መዝሙር 9:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጽዮን ለሚኖር እግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! ያደረገውንም ድንቅ ሥራ ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምህን የሚያውቁ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን ንገሩ፤ |
ከፍልስጥኤም ለሚመጡ መልእክተኞች የምንሰጠው መልስ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና መመሥረቱንና በሥቃይ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቡ መጠጊያ አግኝተው በሰላም እንዲኖሩ ማድረጉን እንነግራቸዋለን።
አንተ እኔን የወደድክበት ፍቅር በእነርሱ ላይ እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን እነርሱ አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ ደግሞም እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ።”
እናንተ ግን ወደ ጽዮን ተራራ ቀርባችኋል፤ እርስዋ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ የሆነችው ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ናት፤ በደስታ ወደተሰበሰቡት፥ በብዙ ሺህ ወደሚቈጠሩት መላእክት ቀርባችኋል።
ከዚህ በኋላ እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ አየሁ፤ ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።