Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህ በኋላ እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ አየሁ፤ ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ ነበር፤ ከርሱም ጋራ የርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራቱ ሺሕ ሰዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚያም አየሁ፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አየሁም፤ እነሆም በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አየሁም፥ እነሆም፥ በጉ በጽዮን ተራራ ቆሞ ነበር፥ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም በግምባራቸው የተጻፈላቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 14:1
30 Referencias Cruzadas  

የእግዚአብሔርንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ከጽዮን ተራራና ከኢየሩሳሌም መዳን ይገኛል፤ ከሚድኑትም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኙበታል።”


ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ፤ ይህችም ከተማ ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት፤ የእኔንም አዲስ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሳያፍር በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ እኔም ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት እመሰክርለታለሁ እላችኋለሁ።


አንካሶች ተርፈው እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤ ተጥለው የነበሩትን ብርቱ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፤ እኔም በጽዮን ተራራ ላይ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በእነርሱ ላይ እነግሣለሁ።”


ይህም፦ “እነሆ፥ ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ ይህም ድንጋይ ሰዎችን በማሰናከል የሚጥል አለት ነው፤ በእርሱ የሚያምን ግን አያፍርም” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


“በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ ንጉሤን ሾምኩ” ይላቸዋል።


ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ፥ ነጭ ደመና አየሁ፤ በደመናው ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፤ በራሱ ላይ የወርቅ አክሊል አድርጎአል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞአል፤


ከዚህም በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ፥ የምስክር ድንኳን የሆነው ቤተ መቅደስ በሰማይ ተከፈተ፤


የኢየሩሳሌም ሕዝብ ግን፥ “እግዚአብሔር ትቶናል፤ ጌታዬም ረስቶናል” አሉ።


እነሆ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ይባል ነበር፤ ሲኦልም ይከተለው ነበር፤ ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ እጅ በጦርነት፥ በራብ፥ በቸነፈርና በምድር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።


ከዚህ በኋላ ተመለከትኩ፤ እነሆ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሰምቼው የነበረው እንደ እምቢልታ ያለው ድምፅ እንዲህ አለ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ ወደፊት መሆን የሚገባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ፤”


“ይህ የምታየው ምንድን ነው?” ብሎም ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፦ “ሰባት መብራቶች ያሉበት አንድ የወርቅ መቅረዝ አያለሁ፤ በአናቱም ላይ የዘይት ማሰሮ አለ፤ ሰባቱም መብራቶች የክር ማስተላለፊያ ቧንቧ አላቸው።


እግዚአብሔርም “ይህ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልኩት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ እነርሱን ከመቅጣት አልመለስም።


ከዚያን በኋላ በወንዝ ዳር ሁለት ሰዎች ማዶ ለማዶ ቆመው አየሁ፤


ከዚያም በኋላ ያ ሰው በሰሜኑ ቅጽር በር በኩል አድርጎ ወደ ቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ወሰደኝ፤ በዚያም ሆኜ ስመለከት የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በክብሩ ተሞልቶ አየሁ፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ፤


ከኪሩቤል ራሶች በላይ ያለውን ጠፈር ተመለከትኩ፤ በኪሩቤል ላይ ከሰንፔር ዕንቊ የተሠራ ዙፋን የሚመስል ነገር አየሁ።


በውጪ በኩል ወዳለው አደባባይ መግቢያ በር ወሰደኝ፤ በቅጽሩ ግንብ ላይ አንድ ቀዳዳ ነበር፤


ከዚህ በኋላ የብራና ጥቅል የያዘ እጅ ወደ እኔ ተዘርግቶ አየሁ።


ቀና ብዬ ስመለከት ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል ሲመጣ አየሁ፤ ከግዙፍ ደመና የመብረቅ ብልጭታ ይታይ ነበር፤ በዙሪያው ያለውም ሰማይ ቀላ፤ መብረቁ በሚበርቅበትም ስፍራ አንዳች ነገር እንደ ነሐስ አበራ።


እግዚአብሔርም “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የለውዝ ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩት።


ስመለከት እያንዳንዱ መንኰራኲር በያንዳንዱ ኪሩብ አጠገብ ሆኖ አራት መንኰራኲሮችን አየሁ፤ የመንኰራኲሮቹም መልክ የሚያንጸባርቅ ዕንቊ ይመስል ነበር።


“በመላዋ ኢየሩሳሌም ከተማ ተዘዋወር፤ በከተማይቱ ከተፈጸመውም አጸያፊና አሳፋሪ ነገር የተነሣ በመሠቀቅ ባዘኑት ሰዎች ግንባር ላይ ምልክት አድርግባቸው!” አለው።


በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች፥ በሽማግሌዎችም ፊት መቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ ይህን መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።


ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም በየግምባራቸው ላይ ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios