መዝሙር 81:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ሆይ! የማስጠንቀቂያ ንግግሬን ስማ! እስራኤል ሆይ! ብታዳምጡኝ ምንኛ መልካም ነበር! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቤ ሆይ፤ ሳስጠነቅቅህ ስማኝ፤ እስራኤል ሆይ፤ ምነው ብታደምጠኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራህ ጊዜ ጠራኸኝ አዳንሁህም፥ ከተሰወረ የሞገድ ስፍራ መለስሁልህ፥ በክርክር ውኃ ዘንድም ፈተንሁህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና። |
እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።
በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ።
ስለዚህ ወደ እርሱ ቀርበህ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ አዳምጥ፤ ተመልሰህም እርሱ ያለውን ሁሉ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እንታዘዛለን።’
ሰዎች የሚሰጡትን ምስክርነት እንቀበላለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ምስክርነት ከሁሉ ይበልጣል። እግዚአብሔር ስለ ልጁ የሰጠውም ምስክርነት ይህ ነው።