ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”
መዝሙር 78:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ሥርዓትን ለያዕቆብ ልጆች ዐወጀ፤ ለእስራኤልም ሕግን መሠረተ፤ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ የቀድሞ አባቶቻችንን አዘዛቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ፤ በእስራኤልም ሕግን ደነገገ፤ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ፣ አባቶቻችንን አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለልጆቻቸው ያስታውቅ ዘንድ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ምስክር በያዕቆብ አቆመ፥ በእስራኤልም ሕግን ሠራ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለህ? ቅንዐትህም እንደ እሳት ይነድዳል? |
ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ቤተሰቡን በመምከር ይመራቸው ዘንድ እኔ እርሱን መርጬዋለሁ፤ ልጆቹ ይህን ካደረጉ እኔም ለአብርሃም የሰጠሁትን ተስፋ ሁሉ እፈጽማለሁ።”
የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ለነፍስ አዲስ ሕይወትን ይሰጣል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ የታመነ ነው፤ ማስተዋል ለጐደላቸው ጥበብን ይሰጣል።
እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሱላቸዋላችሁ፤ ‘ይህ እግዚአብሔርን ለማክበር የሚደረግ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የእስራኤላውያንን መኖሪያ ቤቶች አልፎ በመሄድ ግብጻውያንን ሲገድል እኛን አድኖናል።’ ” እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ፤
ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች ወስዶ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ አስቀመጣቸው፤ መሎጊያዎችንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረ፤
እናንተም ወላጆች ሆይ! በጌታ በኢየሱስ ሥነ ሥርዓትን በማስተማር፥ በማረምና በመገሠጽ አሳድጉአቸው እንጂ ልጆቻችሁን በማስቈጣት አታስመርሩአቸው።
ለልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤ በቤት በምትቀመጡበት ጊዜ፥ ወይም ስትሄዱ፥ ዕረፍት በምታደርጉበትም ሆነ በምትሠሩበት ጊዜ ሁሉ ስለ እነርሱ ተነጋገሩ፤
በዚህም ዐይነት የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ሕግ ሰምተው የማያውቁ ዘሮቻችሁ ሁሉ ሊያዳምጡት ይችላሉ፤ ስለዚህም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር መታዘዝን ይማራሉ።”
እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ።
እነዚህኑ ትእዛዞች ለልጆችህ አስተምራቸው፤ በቤት ስትቀመጥም ሆነ በመንገድ ስትሄድ፥ ዕረፍት በምታደርግበትም ጊዜ ሆነ ሥራ በምትሠራበት ጊዜ ሁሉ፥ እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር አሰላስል፤