“እግዚአብሔር ለዘወትር ይጥለናልን? ከእንግዲህስ ወዲህ ለእኛ ቸርነት አያደርግምን?
“ለመሆኑ፣ ጌታ ለዘላለም ይጥላልን? ከእንግዲህስ ከቶ በጎነትን አያሳይምን?
በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ ነፍሴንም አነቃቃኋት።
ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲፈልጉ፤
እግዚአብሔር በእጁ ስለሚደግፈው ቢደናቀፍም አይወድቅም።
ለእግዚአብሔር ትክክለኛውን መሥዋዕት አቅርቡ፤ እምነታችሁንም በእርሱ ላይ አድርጉ።
አሁን ግን ጣልከን፤ አዋረድከንም፤ ከሚዘምተው ሠራዊታችን ጋር አብረህ መውጣትን ትተሃል።
አምላክ ሆይ! እንደዚህ ለምን ተውከን? ሕዝብህንስ የምትቈጣው ለዘለዓለም ነውን?
እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የምትቈጣው እስከ መቼ ድረስ ነው? ቅናትህ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራልን?
እግዚአብሔር ሆይ! ለምድርህ ምሕረትን አሳየህ፤ የያዕቆብን ዘር እንደገና አበለጸግህ።
በእኛ ላይ የምትቈጣው ለዘለዓለም ነውን? ቊጣህንስ ከትውልድ ወደ ትውልድ ታስተላልፋለህን?
አሁን ግን በመረጥከው ንጉሥ ላይ ተቈጥተሃል፤ ተለይተኸዋል፤ ጥለኸዋልም።
እግዚአብሔር ሆይ! የምትሰወረው ለዘለዓለም ነውን? ቊጣህስ እንደ እሳት የሚነደው እስከ መቼ ነው?