ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ እውነተኛነትህ የስምህንና የትእዛዞችህን ከፍተኛነት ስላሳየህ ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እየሰገድኩ ስምህን አመሰግናለሁ።
መዝሙር 75:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ፥ እናመሰግንሃለን፤ አንተ ወደ እኛ ስለ ቀረብክ ለስምህ ምስጋና እናቀርባለን፤ ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ እንናገራለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ስምህ ቅርብ ነውና ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ሰዎችም ስለ ድንቅ ሥራህ ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። የአሳፍ የምስጋና መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ሆነ። |
ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህና ስለ እውነተኛነትህ የስምህንና የትእዛዞችህን ከፍተኛነት ስላሳየህ ወደ ተቀደሰው ቤተ መቅደስህ እየሰገድኩ ስምህን አመሰግናለሁ።
አምላክ ሆይ! በጥንት ዘመን ያደረግኸውን ሁሉ በጆሮአችን ሰማን፤ የቀድሞ አባቶቻችንም በዘመናቸው ስላደረግሃቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ነግረውናል።
የሚነግርህን በማዳመጥ ለእርሱ ታዘዝ፤ በእርሱም ላይ አታምፅ፤ ለእርሱ ሙሉ ሥልጣን የሰጠሁት ስለ ሆነ የምትፈጽመውን ዐመፅ እየተመለከተ ይቅርታ አያደርግልህም።
“እኛ በምንለምነው ጊዜ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር ለእኛ ቅርብ እንደሆነው፥ የየትኛው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ነው አምላኩ ለእርሱ ቅርብ የሆነለት?