ካህናቱና ሌዋውያኑም ቆመው የእግዚአብሔር በረከት በሕዝቡ ላይ እንዲወርድ ጸለዩ፤ እግዚአብሔርም በተቀደሰ መኖሪያው በሰማይ ሆኖ ጸሎታቸውን ሰማ።
መዝሙር 68:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸውም ሴቶች ጠባቂ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በተቀደሰ ማደሪያው፣ ለድኻ አደጉ አባት፣ ለባልቴቲቱም ተሟጋች ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ፥ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ፥ ስሙ ጌታ ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አንተ ስንፍናዬን ታውቃለህ፥ ኃጢአቴም ከአንተ አልተሰወረም። |
ካህናቱና ሌዋውያኑም ቆመው የእግዚአብሔር በረከት በሕዝቡ ላይ እንዲወርድ ጸለዩ፤ እግዚአብሔርም በተቀደሰ መኖሪያው በሰማይ ሆኖ ጸሎታቸውን ሰማ።
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።
እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
በዚያን ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦ “እግዚአብሔርን አመስግኑ! ስሙንም አክብሩ! በሕዝቦች መካከል እርሱ ያደረገውን ተናገሩ! ስለ ገናናነቱም መስክሩ!
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?
በመካከላችሁ ያሉትን አባቶቻቸውና እናቶቻቸው የሞቱባቸውን ልጆች ተዉአቸው እኔ በሕይወት አኖራቸዋለሁ። ባሎቻቸው የሞቱባቸውም ሴቶች በእኔ ይተማመኑ።
እነርሱ እንደ ቅልብ ሰንጋ ወፍረዋል፤ ክፉ ሥራቸውም ገደብ የለሽ ሆኖአል፤ እናትና አባት የሌላቸውን ልጆች መብት አያስከብሩም፤ ለችግረኞችም ትክክለኛ ፍርድ አይፈርዱም።
አሦር አያድነንም፥ በጦር ፈረሶችም አንታመንም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በእጃችን የሠራነውን ጣዖት ሁሉ ‘አምላክ’ ብለን አንጠራም፤ አምላክ ሆይ! ወላጆቻቸው የሞቱባቸው በአንተ ምሕረትን ያገኛሉ።”
እርሱ እናትና አባት ለሌላቸው ድኻ አደጎችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች በትክክል ይፈርዳል፤ እርሱ በእኛ ሕዝብ መካከል የሚኖሩትንም መጻተኞች ሁሉ ስለሚወድ ምግብና ልብስ ይሰጣቸዋል።
በሰማይ ካለው ቅዱስ መኖሪያህ ሆነህ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንም ባርክ፤ ለቀድሞ አባቶቻችን በገባኸው ቃል መሠረት የሰጠኸንን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለም ምድር ባርክ።’