መዝሙር 67:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓለም በሙሉ የአንተን መንገድ፥ ሕዝቦችም የአንተን አዳኝነት ይወቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገድህ በምድር ላይ፣ ማዳንህም በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይታወቅ ዘንድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም፥ ፊቱንም በላያችን ያብራ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፤ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ኃጥኣን ከአግዚአብሔር ፊት ይጥፉ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
ስለ ጌታ መንገድ የተማረና በመንፈስም የተቃጠለ ሆኖ ስለ ኢየሱስ በትክክል ይሰብክና ያስተምር ነበር፤ ይሁን እንጂ እርሱ የሚያውቀው የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ ነበር።
የክርስትናን እምነት የሚከተሉትን ሁሉ እስከ ሞት የማሳድድ ሰው ነበርኩ፤ ወንዶችንና ሴቶችን እያሰርኩ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አደርግ ነበርኩ።
በይሁዳ፥ በገሊላና በሰማርያ ሁሉ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሰላም አገኘች፤ በረታችም፤ ጌታን እያከበረችና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናናች በቊጥር አደገች።