መዝሙር 66:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ብር በእሳት ተፈትኖ እንደሚጠራ ፈተንከን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤ እንደ ብርም አነጠርኸን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ፈትነኸናልና፥ ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና። |
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”
እርሱ እንደ ብረት አቅላጭና እንደ ብር አንጥረኛ ፍርድን ለማጣራት ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች የጽድቅ መሥዋዕት ለማቅረብ እስከሚችሉ ድረስ እንደ ወርቅና እንደ ብር ያጠራቸዋል።
አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዞች ስለ መጠበቅህ በልብህ ያለውን ሐሳብ ያውቅ ዘንድ አንተን ለመፈተን በዚህ በረሓ አርባ ዓመት ሙሉ በመከራ ውስጥ በማሳለፍ እንዴት እንደ መራህ አስታውስ።